በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 13, 2019
አውስትራሊያ

ሰደድ እሳት በአውስትራሊያ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ

ሰደድ እሳት በአውስትራሊያ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ

አውስትራሊያ ውስጥ በኒው ሳውዝ ዌልስና በኩዊንስላንድ የተነሳው ሰደድ እሳት ከአንድ ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሚሆን ቦታ አውድሟል፤ የይሖዋ ምሥክር የሆኑ አንድ ባልና ሚስት በዚህ አደጋ ምክንያት ቤታቸውን አጥተዋል። በእሳት አደጋው ምክንያት የተጎዳም ሆነ ሕይወቱን ያጣ አንድም የይሖዋ ምሥክር የለም። የጉባኤና የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾችም ከአደጋው ተርፈዋል።

የአካባቢው ባለሥልጣናት እሳቱን ሰዎች ሆን ብለው እንዳስነሱት ያምናሉ። ከመስከረም አንስቶ በእሳቱ ምክንያት ስድስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ቢያንስ 650 ቤቶች ወድመዋል።

ወደ 200 ገደማ የሚሆኑ ወንድሞችና እህቶች አካባቢውን ለቀው መሄድ አስፈልጓቸው የነበረ ቢሆንም አሁን ወደየቤታቸው ተመልሰዋል። ቤታቸው የተቃጠለባቸውን ባልና ሚስት ደግሞ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች እየተንከባከቧቸው ነው። የጉባኤ ሽማግሌዎች አደጋ በደረሰበት አካባቢ ለሚኖሩት ወንድሞች መንፈሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው።—የሐዋርያት ሥራ 20:28