በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 3, 2021
ኢንዶኔዥያ

በኢንዶኔዥያ የተከሰተ ኃይለኛ ጎርፍ

በኢንዶኔዥያ የተከሰተ ኃይለኛ ጎርፍ

ቦታ

ደቡብ ካሊማንታን፣ ሰሜን ሱላዌሲ እና ሰሜን ማለከስ

የደረሰው አደጋ

  • ጥር 2021 አጋማሽ ላይ የተከሰተው ኃይለኛ የጎርፍ መጥለቅለቅና የመሬት መንሸራተት መጠነ ሰፊ ጉዳት አስከትሏል፤ እንዲሁም ብዙዎች ከመኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 90 ገደማ የሚሆኑ አስፋፊዎች ለጊዜው ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 3 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የጉባኤ ሽማግሌዎች አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ አስፋፊዎቹ አደጋ የደረሰበትን አካባቢ ለቅቀው እንዲወጡ ረድተዋቸዋል። በተጨማሪም አስፋፊዎቹ ጊዜያዊ መኖሪያ፣ ምግብና ሌሎች መሠረታዊ ነገሮችን እንዲያገኙ ሽማግሌዎቹ ረድተዋቸዋል

  • በአካባቢው ባለው ጉባኤ ያሉት አስፋፊዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች በማጽዳቱና በመጠገኑ ሥራ እርዳታ እያበረከቱ ነው

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአደጋው ለተጎዱት አስፋፊዎች መንፈሳዊ ድጋፍና ማበረታቻ እየሰጡ ነው

  • ሁሉም የእርዳታ ሥራዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ይሖዋ ‘በመከራ ቀን’ እርዳታ የሚያበረክት አፍቃሪ የወንድማማች ማኅበር ስለሰጠን እናመሰግነዋለን።—ምሳሌ 17:17