በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኢንዶኔዥያን የመታው ርዕደ መሬት ብዙ ውድመት አድርሷል

ኅዳር 23, 2022
ኢንዶኔዥያ

ኢንዶኔዥያ በርዕደ መሬት ተመታች

ኢንዶኔዥያ በርዕደ መሬት ተመታች

ኅዳር 21, 2022 ኢንዶኔዥያ በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 5.6 በተመዘገበ ርዕደ መሬት ተመታች፤ ርዕደ መሬቱ የተከሰተው በዌስት ጃቫ በምትገኘው በሲያንጁር ከተማ ነው። የመሬት መንቀጥቀጡ ከ260 በላይ ሰዎችን ለሞት፣ መቶዎችን ደግሞ ለአካል ጉዳት ዳርጓል። በርካቶች የት እንደገቡ አልታወቀም፤ ሺዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። በመላ አገሪቱ የኃይል መቆራረጥ ስለተከሰተ መረጃ መለዋወጥ አስቸጋሪ ሆኗል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችን መካከል በአደጋው ሕይወቱን ያጣ የለም፤ አደጋው በደረሰበት አካባቢ ካሉ 132 አስፋፊዎችም አንድም የጠፋ የለም

  • 5 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ ወይም የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ የለም

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • ዋናውን ርዕደ መሬት ተከትሎ የሚከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ካለ አረጋውያንን የሚያግዙ አስፋፊዎች እንዲመደቡ ዝግጅት ተደርጓል

  • የአደጋ ጊዜ የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ጉባኤዎቹን እንዲያግዝ ተመድቧል

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ጉዳት የደረሰባቸውን ጉባኤዎች በመጎብኘት መንፈሳዊ ማበረታቻ እየሰጡ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

በዚህ አስጨናቂ ወቅት ይሖዋ ወንድሞቻችንን እንደሚያጽናናቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 50:15