ሰኔ 24, 2019
ኢኳዶር
ጉዋያኪል፣ ኢኳዶር—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከሰኔ 14-16, 2019
ቦታ፦ ኤስታዲዮ ሞንዩሜንታል ባንኮ ፒቺንቻህ፣ ጉዋያኪል፣ ኢኳዶር
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ የኢኳዶር ምልክት ቋንቋ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 53,055
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 702
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,300
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ምያንማር፣ ሞልዶቫ፣ ስፔን፣ ቤልጅየም፣ ቦሊቪያ፣ አርጀንቲና፣ ኩባ፣ ካዛክስታን፣ ኮሎምቢያ፣ ኮሪያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፖላንድ
ተሞክሮ፦ የስታዲየሙ ባለቤት የሆነው የባርሴሎና የስፖርት ክለብ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሆሴ ፍራንሲስኮ ሲቫዮስ እንዲህ ብለዋል፦ “ዘንድሮም ሆነ ባለፉት ዓመታት ባደረጋችኋቸው ስብሰባዎች ላይ ምንም ችግር አጋጥሞን አያውቅም። መልካም ባሕርይ እንዳላችሁና የተደራጃችሁ እንደሆናችሁ ከስብሰባዎቻችሁ በግልጽ ማየት ችለናል። ቀላል ባይሆንም እንኳ ሁሌም ለስብሰባዎቻችሁ ጥሩ ዝግጅት ታደርጋላችሁ እንዲሁም በደንብ የተደራጃችሁ ናችሁ። የተማራችሁ፣ መልካም ምግባር ያላችሁና የተደራጃችሁ ጥሩ ሰዎች ናችሁ። የትኛውም ከተማ አልፎ ተርፎም የትኛውም አገር እናንተን እንዲያስተናግድ እናበረታታለን።”
የኢኳዶርን ቤቴል እየጎበኙ ያሉ ልዑካን ፎቶግራፍ ሲነሱ
በአካባቢው ያሉ ወንድሞችና እህቶች ከልዑካኑ ጋር ሲያገለግሉ
ከተለያዩ አገራት የመጡ ልዑካን በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ላይ በኅብረት ሲዘምሩ
በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 702 ወንድሞችና እህቶች መካከል የተወሰኑት
ልዑካኑ ስብሰባው ላይ ማስታወሻ ሲጽፉ
ልዑካኑ፣ ኮሪያውያን ፍቅርን ለማመልከት የሚጠቀሙበትን ምልክት በእጃቸው ሲያሳዩ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ኬነዝ ኩክ የቅዳሜን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ
ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ላይ ሕዝቡን ሲሰናበቱ
የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ልዑካኑን በተለያዩ ትርዒቶች ሲያዝናኑ