በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኤርትራ

ታሪካዊ ኩነቶች—ኤርትራ

ታሪካዊ ኩነቶች—ኤርትራ
  1. ሚያዝያ 2014—ባለሥልጣናት ሃይማኖታዊ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከ120 በላይ የይሖዋ ምሥክሮችን (ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች) አሰሩ፤ አብዛኞቹ ወዲያውኑ ተለቀቁ

  2. ሐምሌ 8, 2008—ባለሥልጣናት ቤቶችንና የሥራ ቦታዎችን በመፈተሽ 24 የይሖዋ ምሥክሮችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ

  3. ግንቦት 2002—መንግሥት፣ ፈቃድ ከተሰጣቸው አራት ሃይማኖቶች በስተቀር ሁሉንም የሃይማኖት ቡድኖች አገደ

  4. ጥቅምት 25, 1994—የይሖዋ ምሥክሮች ዜግነታቸውንና መሠረታዊ የሲቪል መብቶቻቸውን እንዲነጠቁ የሚያደርግ ፕሬዚዳንታዊ ድንጋጌ ወጣ

  5. መስከረም 17, 1994—ባለሥልጣናት፣ ጳውሎስ ኢያሱን፣ ይስሐቅ ሞገስን እና ነገደ ተክለማርያምን ያለክስ አሰሩ

  6. 1994—ባለሥልጣናት የይሖዋ ምሥክሮችን እየያዙ ማሰር ጀመሩ

  7. ሚያዝያ 27, 1993—ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አወጀች

  8. 1954—አነስተኛ የይሖዋ ምሥክሮች ቡድን በተደራጀ መንገድ አምልኮ ማከናወን ጀመረ