በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 4, 2020
ኤርትራ

ኤርትራ 28 የይሖዋ ምሥክሮችን ከእስር ለቀቀች

ኤርትራ 28 የይሖዋ ምሥክሮችን ከእስር ለቀቀች

ታኅሣሥ 4, 2020 በኤርትራ በእምነታቸው ምክንያት ታስረው የነበሩ 26 ወንድሞችና 2 እህቶች ከእስር ተለቀቁ። እነዚህ ወንድሞችና እህቶች ከ5 እስከ 26 ለሚደርሱ ዓመታት እስር ቤት ቆይተዋል። ሁሉም ለይሖዋ አምላክ ጽኑ ታማኝነት አሳይተዋል። ዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን በዚህ ዜና እጅግ ተደስቷል። እርግጥ ነው፣ አሁንም ኤርትራ ውስጥ በእስር ላይ ያሉትን 24 ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ማሰባችንን እንዲሁም ስለ እነሱ መጸለያችንን አናቋርጥም!—የሐዋርያት ሥራ 12:5