በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 29, 2021
ኤርትራ

የኤርትራ ባለሥልጣናት ሌላ የይሖዋ ምሥክር ከእስር ለቀቁ

የኤርትራ ባለሥልጣናት ሌላ የይሖዋ ምሥክር ከእስር ለቀቁ

ኤርትራ ውስጥ በእምነቱ ምክንያት ከ12 ዓመት በላይ ታስሮ የነበረ አንድ ወንድማችን ጥር 29, 2021 ከእስር ተለቅቋል። ታኅሣሥ 4, 2020 28 የይሖዋ ምሥክሮች ከእስር ተለቀው ነበር። ወንድሞቻችን ከእስር በመለቀቃቸው በጣም ተደስተናል። በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ውስጥ በእስር ላይ ለሚገኙት 23 ወንድሞችና እህቶችም መጸለያችንን እንቀጥላለን።—ዕብራውያን 13:3