ግንቦት 21, 2021
እስራኤል
በእስራኤል እና በፍልስጤም ግዛት የተፈጠረ ግጭት
ቦታ
እስራኤል እና የፍልስጤም ግዛት
የደረሰው አደጋ
ግንቦት 10, 2021 በእስራኤልና በፍልስጤም ግዛት ግጭት ተነስቶ ነበር፤ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል
አይሁዳውያንና አረቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው የእስራኤል ከተሞች ውስጥ በግለሰብና በሕዝብ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
በእስራኤል እና በፍልስጤም ግዛት ከሚኖሩት ከ2,000 የሚበልጡ አስፋፊዎች መካከል አንዳቸውም አካላዊ ጉዳት አልደረሰባቸውም
መስክ ላይ የሚያገለግሉ 15 የልዩ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችን ጨምሮ 73 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። 13 ቤቴላውያን የቦንብ ጥቃት መከላከያ ባላቸው አፓርትመንቶች ውስጥ ለጊዜው መጠለል አስፈልጓቸው ነበር
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
6 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው የእርዳታ ሥራውን እያቀናጀ ሲሆን ከወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ከአካባቢው የጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመሆን አስፈላጊውን እርዳታ እያቀረበ ነው
በተጨማሪም የወረዳ የበላይ ተመልካቾቹ ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር ለአስፋፊዎች መንፈሳዊ እርዳታ እያደረጉ ነው
ሁሉም የእርዳታ ሥራዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
በአሁኑ ወቅት ሁሉም ስብሰባዎች የሚደረጉት በቪዲዮ ኮንፍረንስ አማካኝነት ስለሆነ የጉባኤ ስብሰባዎች ሳይቋረጡ መቀጠል ችለዋል። ግንቦት 15 ወንድሞችና እህቶች የወረዳ ስብሰባቸውን በJW ስትሪም ስቱዲዮ አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት መከታተል ችለዋል። የከሰዓት በኋላው ፕሮግራም ባለሥልጣናቱ የማስጠንቀቂያ ደወል በማሰማታቸው ምክንያት ሦስት ጊዜ ተቋርጦ ነበር። ወንድሞች እነዚህን ደወሎች ሲሰሙ ከለላ ለማግኘት ከደረጃ በታች ባለው ቦታ ወይም የቦንብ ጥቃት መከላከያ ውስጥ ይጠለላሉ። ግጭቱ ቢኖርም እንኳ 804 አስፋፊዎች በዕብራይስጥ የተላለፈውን ፕሮግራም ተከታትለዋል። በተጨማሪም 297 አስፋፊዎች በታጋሎግ ቋንቋ የተደረገውን የወረዳ ስብሰባ ተከታትለዋል። በእስራኤል እና በፍልስጤም ግዛት የሚገኙት አምስት የአረብኛ ጉባኤዎች ግንቦት 22 የወረዳ ስብሰባ ያደርጋሉ።
በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በይሖዋ መተማመናቸውንና እሱን መጠጊያቸው ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።—መዝሙር 91:1, 2, 5