በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኦስካር የተባለው አውሎ ነፋስ በማካምቦ፣ ሳን አንቶኒዮ ዴል ሱር፣ ኩባ የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን የስብሰባ ቦታ ሙሉ በሙሉ አውድሟል

ኅዳር 6, 2024
ኩባ

ኦስካር የተባለው አውሎ ነፋስ በኩባ ጉዳት አስከተለ

ኦስካር የተባለው አውሎ ነፋስ በኩባ ጉዳት አስከተለ

ጥቅምት 20, 2024 ኦስካር የተባለው አውሎ ነፋስ፣ በኩባ ምሥራቃዊ ክልል ጓንታናሞ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ባራኮአ ከተማን መትቷል። እርከን 1 ደረጃ የተሰጠውና በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር የሚጓዘው ይህ አውሎ ነፋስ፣ በክልሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በኩባ ምሥራቃዊ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ እስከ 38 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ዝናብ በመዝነቡ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቦታዎች ከመጥለቅለቃቸው በተጨማሪ ሰብል ተበላሽቷል። ቁጥራቸው ከ2,000 የማያንስ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ቤቶችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • አንዲት በዕድሜ የገፉ እህት ሕይወታቸውን ማጣታቸው አሳዝኖናል

  • 2 አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 14 አስፋፊዎች አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርጓል

  • 13 ቤቶች ወድመዋል፤ ከወደሙት ቤቶች መካከል 2ቱ ለጉባኤ ስብሰባዎች ያገለግሉ ነበር

  • 22 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 5 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የቅርንጫፍ ቢሮው ተወካዮች፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የአካባቢው ሽማግሌዎች መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው

  • 2 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመው የእርዳታ እንቅስቃሴዎችን እያስተባበሩ ይገኛሉ

ይህ አውሎ ነፋስ ባደረሰው ውድመትና የሰው ሕይወት በመጥፋቱ ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶናል። ሆኖም የሰማዩ አባታችን ይሖዋ፣ የሚታመኑበትን ሁሉ እንደሚያበረታቸው እርግጠኞች ነን።​—መዝሙር 55:22