በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 5, 2019
ካሜሩን

የይሖዋ ምሥክሮች ካሜሩን ውስጥ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍትን በባሳ ቋንቋ አወጡ

የይሖዋ ምሥክሮች ካሜሩን ውስጥ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍትን በባሳ ቋንቋ አወጡ

ነሐሴ 2, 2019 የይሖዋ ምሥክሮች በዶዋላ፣ ካሜሩን በተደረገ የክልል ስብሰባ ላይ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉምን በባሳ ቋንቋ አውጥተዋል። ይህን ትርጉም ለማዘጋጀት አንድ ዓመት ከስድስት ወር ወስዷል። የይሖዋ ምሥክሮች በካሜሩን አገር በቀል ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን ሲተረጉሙ ይህ የመጀመሪያቸው ነው።

የካሜሩን የቅርንጫፍ ቢሮ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ፒተር ካኒንግ በሎግበሱ የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ በተደረገው የክልል ስብሰባ የመጀመሪያ ቀን ላይ 2,015 ለሚሆኑ ተሰብሳቢዎች መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን አብስሯል።

ይህ ትርጉም ከመውጣቱ በፊት የባሳ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች ለመረዳት ከባድና ዋጋው ውድ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይጠቀሙ ነበር። በሥራው ላይ ከተካፈሉት ተርጓሚዎች አንዱ እንዲህ ብሏል፦ “ይህ አዲስ ትርጉም አስፋፊዎች መጽሐፍ ቅዱስን በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል። ለይሖዋና ለድርጅቱ ያላቸውን ፍቅርም ያሳድግላቸዋል።

ካሜሩን ውስጥ 300,000 የሚያህሉ የባሳ ቋንቋ ተናጋሪዎች አሉ። በተጨማሪም በካሜሩን የቅርንጫፍ ቢሮ ክልል ውስጥ የሚያገለግሉ 1,909 የባሳ ቋንቋ ተናጋሪ አስፋፊዎች አሉ።

ይህ ትክክለኛና ለመረዳት ቀላል የሆነ ትርጉም አንባቢዎች “የአምላክ ቃል ሕያው” መሆኑን እንዲገነዘቡ እንደሚረዳቸው እርግጠኞች ነን።—ዕብራውያን 4:12