በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 26, 2019
ካናዳ

ቶሮንቶ፣ ካናዳ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ቶሮንቶ፣ ካናዳ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከሐምሌ 19-21, 2019

  • ቦታ፦ በቶሮንቶ፣ ኦንታሪዮ፣ ካናዳ የሚገኘው የኤግዚቢሽን ማዕከል

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፖርቱጋልኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 46,183

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 317

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,000

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሕንድ፣ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ብራዚል፣ ኮሪያ፣ ፊንላንድ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዩክሬን፣ ጃፓን፣ ፊሊፒንስ

  • ተሞክሮ፦ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ የሽያጭና የፕሮግራም ዝግጅት ኃላፊ የሆነችው ሎራ ፐርዲ እንዲህ ብላለች፦ “የብሔራት አቀፍ ስብሰባው ኮሚቴ፣ ስብሰባው በዚህ አዳራሽ መካሄዱ ስለሚያስገኘው ጥቅም የተናገረው ነገር በሙሉ በትክክል ተፈጽሟል። እኛም ስለ ጉዳዩ አጣርተን ነበር፤ እንዲሁም ስብሰባ የተካሄደባቸውን ሌሎች አዳራሾች ጠይቀናል። የሁሉም ስሜት ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ነው።” አክላም እንዲህ ብላለች፦ “ስብሰባው ሞቅ ያለ መንፈስ ነበረው። ሌሎች አዳራሾችም የይሖዋ ምሥክሮችን ስብሰባ የማስተናገድ አጋጣሚ ካገኙ እንዲጠቀሙበት አበረታታቸዋለሁ።”

 

ወንድሞችና እህቶች አውሮፕላን ማረፊያ ሄደው ወደ ቶሮንቶ የመጡትን ልዑካን ሲቀበሉ

ልዑካኑ ከአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ጋር ሲያገለግሉ

ልዑካኑ የካናዳን ቅርንጫፍ ቢሮ ሲጎበኙ ቤቴላውያን ሙዚቃ እየተጫወቱላቸው

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጄፍሪ ጃክሰን የዓርብ ዕለቱን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ቅዳሜ ዕለት ከተጠመቁት 317 ወንድሞችና እህቶች መካከል አንዱ

ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ወቅት ማስታወሻ ሲይዙ

ሚስዮናውያንና ሌሎች የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ተሰብሳቢዎች እያጨበጨቡላቸው ወደ አዳራሹ ፊት ሲሄዱ

አምስት እህቶች በ1920ዎቹ በቶሮንቶ፣ ካናዳ ከነበረው CKCX የተባለ የሬዲዮ ጣቢያ የሚተላለፈውን ፕሮግራም በተውኔት መልክ ሲያሳዩ። የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች (በወቅቱ የይሖዋ ምሥክሮች የሚጠሩበት ስም ነው) በ1926 በአራት የካናዳ ከተሞች ውስጥ የራሳቸው የሬዲዮ ጣቢያዎች ነበሯቸው፤ ይህም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የካናዳ ቲኦክራሲያዊ ታሪክ ክፍል ነው

ለልዑካኑ ከተዘጋጁት በርካታ ልዩ ፕሮግራሞች በአንዱ ላይ አንድ ወንድም ልጆችን መዝሙር ሲያዘምር