በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አቅኚዎች የሆኑት ወንድም ሙዳሄራንዋ እና ባለቤቱ ወደ ሥራ ሲሄዱ

ሚያዝያ 6, 2020
ካናዳ

ውጥረት በነገሠበት ዘመን ሰላም ማግኘት

ውጥረት በነገሠበት ዘመን ሰላም ማግኘት

በሞንትሪያል፣ ካናዳ የሚኖሩት ወንድም ዣንዬቭስ ሙዳሄራንዋ እና ባለቤቱ እህት ቫስቲ ሙዳሄራንዋ የኮሮና ቫይረስ ሕክምና በመስጠቱ ሥራ ይካፈላሉ። ወንድም ሙዳሄራንዋ ሆስፒታል ውስጥ የመተንፈሻ አካላት ሐኪም ሆኖ ይሠራል፤ እህት ሙዳሄራንዋ ደግሞ የኮቪድ-19 ሕክምና በሚሰጥበት ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት ትሠራለች። እነዚህ ባልና ሚስት ውጥረት በነገሠበት በዚህ ወቅት ከይሖዋ ብርታትና ‘የልብ ደስታ’ አግኝተዋል።—ኢሳይያስ 65:14

ወንድም ሙዳሄራንዋ “ብዙዎቹ የሥራ ባልደረቦቼ በፍርሃት ተውጠዋል፤ እንደዚህ ፈርተው አይቻቸው አላውቅም” ብሏል። እህት ሙዳሄራንዋ ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “የግል ጥናት በጣም ረድቶናል። በመጨረሻው ዘመን ምልክት ላይ እናሰላስላለን፤ ይሖዋ አብሮን እንደሆነና መቼም እንደማይተወን ለማስታወስ እንሞክራለን። ጸሎትም በጣም አስፈላጊ ነው። ሥራ ከመሄዴ በፊት እጸልያለሁ፤ ከዚያም የአእምሮ ሰላም አገኛለሁ።”

ወንድም ሙዳሄራንዋ እና ባለቤቱ በጉባኤ ስብሰባ ሲካፈሉ

ወንድም ሙዳሄራንዋ እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ “የመጣሁት ከሩዋንዳ ነው፤ በዘር ጭፍጨፋው ወቅት እዚያ ነበርኩ። ካናዳ ውስጥ እንደዚያ ያለ ነገር አጋጥሞን አያውቅም፤ ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ በመጨረሻው ዘመን ውስጥ መኖራችንን ልንረሳው እንችላለን። እውነቱን ለመናገር እኔም ብሆን የይሖዋን ቀን አቅርቤ ማየት የተቸገርኩባቸው ጊዜያት ነበሩ። ወረርሽኙ በመጨረሻው ዘመን ውስጥ እንደምንኖር ይበልጥ እርግጠኛ እንድሆን አድርጎኛል፤ እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስና በውስጡ ባሉት ትንቢቶች ላይ ያለኝን እምነት አጠናክሮታል።”

በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ሕዝቦች እንደ ወንድም ሙዳሄራንዋ እና እንደ ባለቤቱ ዓይነት እምነት ስላላቸው በዚህ አስጨናቂ ወቅት ሰላማቸውን ጠብቀው ይኖራሉ።—ኢሳይያስ 48:18