በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ በሉቡምባሺ ከሚገነቡት አዲስ የቢሮ ሕንፃዎች አንዱን የሚያሳይ ሥዕል

ጥር 21, 2022
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አዳዲስ የቤቴል ሕንፃዎች እየተገነቡ ነው

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ አዳዲስ የቤቴል ሕንፃዎች እየተገነቡ ነው

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ በሉቡምባሺ አዲስ የቤቴል ሕንፃ እየተገነባ ነው፤ ይህ ሕንፃ ዋና ቅርንጫፍ ቢሮ ሆኖ ያገለግላል። ግንቦት 2022 260 የሚያህሉ ቤቴላውያን ወደዚህ ሕንፃ መዛወር እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፤ 131 ቤቴላውያን ደግሞ በኪንሻሳ በሚገኘው የአሁኑ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ይቆያሉ። a በተጨማሪም ኪንሻሳ ውስጥ ካለው የአሁኑ ቅርንጫፍ ቢሮ አቅራቢያ ተጨማሪ የመኖሪያ እና የቢሮ ሕንፃ እየተገነባ ነው። ከጥር 2024 በኋላ 48 ገደማ ቤቴላውያን ወደዚህ ሕንፃ እንደሚዛወሩ ይጠበቃል። ሁለቱም ሕንፃዎች በፍጥነት እያደገ ያለውን የኮንጎ ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴ ይደግፋሉ።

ከሦስቱ አዳዲስ የቢሮ ሕንፃዎች የመጀመሪያው ሕንፃ እየተገነባ ነው

በ2021 የአገልግሎት ዓመት በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ያሉ ወንድሞቻችን ከ250,000 የሚበልጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን መርተዋል። በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ላይ ደግሞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተገኝተዋል። በአሁኑ ወቅት በኪንሻሳ በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ የሚያገለግሉ 394 ቤቴላውያን ይገኛሉ።

በኪንሻሳ የሚገኘውን ቤቴል ማስፋፋት ስላልተቻለ ወንድሞች በሌሎች ከተሞች አመቺ ቦታ መፈለግ ጀመሩ። ከዚያም አዲስ ቤቴል ለመገንባትና ወደፊትም እንደ አስፈላጊነቱ ለማስፋፋት የሚያስችል መሬት በሉቡምባሺ አገኙ።

በስተ ግራ፦ ወደ 300 የሚጠጉ ቤቴላውያን በሉቡምባሺ ወደሚገኘው አዲስ የመኖሪያ ሕንፃ በቅርቡ መዛወር ይጀምራሉ። በስተ ቀኝ፦ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ሥዕል

በሉቡምባሺ የተገዛው መሬት የሚገኘው ከኪንሻሳ 2,300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው። መሬቱ 12 ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን መኖሪያዎች፣ ቢሮዎች፣ መጋዘን እንዲሁም መመገቢያ አዳራሽና መዝናኛ ቦታ ያለው ለተለያየ ዓላማ ሊውል የሚችል ሕንፃ ያካትታል።

ግንባታው የጀመረው ኅዳር 2020 ቢሆንም ፕሮጀክቱ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ ብዙ መሰናክሎች አጋጥመውታል።

የኮንጎ (ኪንሻሳ) ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ሮበርት ኢሎንጎ እንዲህ ብሏል፦ “ድንበሮች ተዘግተው ነበር። የግንባታ መሣሪያዎች አቅርቦትም በእጅጉ ተስተጓጉሏል፤ ይህም በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።”

ያም ቢሆን፣ ወንድም ኢሎንጎ እንደገለጸው “በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ 40 በመቶ ተጠናቀቀ።”

ይሖዋ ፕሮጀክቱን እየባረከው እንዳለ በግልጽ ማየት ይቻላል። የክርስቶስ ንብረት ክፍል የሆነው ይህ ሕንፃ፣ ሰዎች ለይሖዋ ሕዝቦች አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው የሚያደርግ እንዲሁም ለይሖዋ አምላክ ስም ክብር የሚያመጣ እንዲሆን እንጸልያለን።—ማቴዎስ 24:47

a የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ (ኪንሻሳ) ቅርንጫፍ ቢሮ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ እና በኮንጎ ሪፑብሊክ የሚካሄደውን ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴ ይከታተላል