በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 21, 2022
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

አውዳሚ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት በኮንጎ (ኪንሻሳ) ጉዳት አደረሰ

አውዳሚ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት በኮንጎ (ኪንሻሳ) ጉዳት አደረሰ

ታኅሣሥ 13, 2022 የጣለው ከባድ ዝናብ ኮንጎ (ኪንሻሳ) ውስጥ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል። በጎርፍ መጥለቅለቁና በሕንፃዎች መፍረስ ምክንያት ቢያንስ 141 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • የሚያሳዝነው፣ 1 ወንድም ሕይወቱን አጥቷል

  • 1 አስፋፊ ጉዳት ደርሶበታል

  • 3 ቤቶች ወድመዋል

  • 3 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 5 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች እረኝነት እያደረጉና ተግባራዊ እገዛ እየሰጡ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን እንዲያስተባብሩ 3 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ኢየሱስ ክርስቶስ የምድርን ተፈጥሯዊ ኃይሎች የሚቆጣጠርበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን፤ ያ ጊዜ ምድራችንም ሆነች የሰው ዘር ታላቅ ጸጥታና እረፍት የሚያገኙበት ጊዜ ይሆናል።—ማቴዎስ 8:25-27