ሰኔ 3, 2021
ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ
ኮንጎ ውስጥ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በአሉር ቋንቋ ወጣ
ግንቦት 30, 2021 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በአሉር ቋንቋ ወጣ። የኮንጎ (ኪንሻሳ) ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ሂዩግ ካቢትሿ መጽሐፍ ቅዱሱ በዲጂታል ፎርማት መውጣቱን አስቀድሞ በተቀረጸ ንግግር አማካኝነት አብስሯል።
አጭር መረጃ
አሉር በማዕከላዊ አፍሪካ፣ በተለይም በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሰሜን ምሥራቃዊ ክፍል እና በአጎራባቿ በኡጋንዳ የሚነገር ቋንቋ ነው
1,735,000 ያህል ሰዎች የአሉር ቋንቋን እንደሚናገሩ ይገመታል
የአሉር ቋንቋን በሚጠቀሙ 48 ጉባኤዎችና ቡድኖች ውስጥ የሚያገለግሉ ከ1,500 የሚበልጡ አስፋፊዎች አሉ
በሥራው የተካፈሉት 6 ተርጓሚዎች ሥራውን ለማጠናቀቅ 12 ወራት ፈጅቶባቸዋል
የኮንጎ (ኪንሻሳ) ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ክሪስቲያን ቤሎቲ እንዲህ ብሏል፦ “የአሉር ቋንቋን የሚጠቀሙ አስፋፊዎች ይህን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ እንደሚያስደስታቸው አልጠራጠርም። ቅዱሳን መጻሕፍትን ለማብራራትና ሌሎች ለአምላክ ቃል ልባዊ አድናቆት እንዲያድርባቸው ለመርዳት ያግዛቸዋል።”—ሉቃስ 24:32
ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘የዘላለሙን ምሥራች’ ማወጃቸውን እንዲቀጥሉ እንደሚረዳቸው እርግጠኞች ነን።—ራእይ 14:6