ሚያዝያ 19, 2021
ዓለም አቀፋዊ ዜና
ሴሮጃ የተባለው አውሎ ነፋስ ኢንዶኔዥያን እና ቲሞር ሌስተን መታ
ቦታ
በምሥራቅ ኢንዶኔዥያ የሚገኙት የኢስት ኑሳ ቴንጋራ ደሴቶች እና ቲሞር ሌስተ
የደረሰው አደጋ
ሚያዝያ 4, 2021 ሴሮጃ የተባለው አውሎ ነፋስ ከባድ ውድመት ያስከተለ ከመሆኑም ሌላ ብዙዎችን ከመኖሪያቸው አፈናቅሏል
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ቢያንስ 236 ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
ኢንዶኔዥያ
45 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
8 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
3 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
ቲሞር ሌስተ
19 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
10 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የእርዳታ ሥራውን ለማስተባበር በኢንዶኔዥያ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል። ኮሚቴው በተጎዱ የስብሰባ አዳራሾችና ከባድ ጉዳት በደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶች ላይ የጥገና ሥራ እንዲከናወን እያስተባበረ ነው
በአካባቢው ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞችና እህቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚያጽናና ሐሳብ እያካፈሏቸው ነው
አውሎ ነፋሱ ከተከሰተ ብዙም ሳይቆይ የጉባኤ ሽማግሌዎች ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ወንድሞችና እህቶች መጠለያ አዘጋጁ። በተጨማሪም ምግብ፣ ውኃና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን አቀረቡ። ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች የማጽዳቱንም ሥራ አስተባብረዋል
በቲሞር ሌስተ ሽማግሌዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች ማጽዳት እንዲሁም ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ማቅረብ ጀምረዋል። በተጨማሪም ለተፈናቀሉት ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያ አዘጋጅተዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
ይሖዋ የክርስቲያን ጉባኤ በሚያከናውነው “የእርዳታ አገልግሎት” አማካኝነት ወንድሞችን እየደገፈ በመሆኑ አመስጋኞች ነን።—2 ቆሮንቶስ 9:13