የካቲት 19, 2020
ዓለም አቀፋዊ ዜና
በምልክት ቋንቋ አፕሊኬሽናችን ላይ የወጣ አዲስ ገጽታ
የካቲት 15, 2020 በወጣው የJW Library Sign Language አፕሊኬሽን 4ኛ ሥሪት ላይ አዲስ ገጽታ ተካትቷል። የምልክት ቋንቋ ተጠቃሚዎች አንዴ ጠቅ በማድረግ ወይም በመጫን ብቻ የማመሣከሪያ ጽሑፎችን ቪዲዮ ማየት ይችላሉ፤ ይህም ለጉባኤ ስብሰባዎች መዘጋጀትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምርምር ማድረግ ቀላል እንዲሆንላቸው ያደርጋል።
የJW Library ተጠቃሚዎች ከድሮም ጀምሮ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ወደ ሌሎች ጽሑፎች የሚመሩ ሊንኮችን የነበሩበትን ገጽ ሳይለቁ መክፈት ይችሉ ነበር። ሆኖም ከምልክት ቋንቋ ጋር በተያያዘ እንዲህ ማድረግ አስቸጋሪ ነበር፤ ምክንያቱም በቪዲዮ ከተዘጋጀ ጽሑፍ ወደ ማመሣከሪያ በቀጥታ መሄድ አስቸጋሪ ነው።
የJW Library Sign Language አፕሊኬሽን 4ኛ ሥሪት ላይ ማመሣከሪያዎቹ በሊንክ መልክ እንዲቀመጡ ተደርጓል። ተጠቃሚዎች አንዴ ጠቅ በማድረግ ብቻ ተጨማሪ ማመሣከሪያ ቪዲዮዎችን ከተመለከቱ በኋላ በቀላሉ ወደ ዋናው ቪዲዮ መመለስ ይችላሉ።
ለሳምንቱ መሃል ስብሰባ የተዘጋጁ ማመሣከሪያዎችን መመልከት ምን ያህል ቀላል እንደሆነ ተመልከት
ይህ አዲስ ገጽታ የምልክት ቋንቋ ቪዲዮዎችን የሚጠቀሙ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን በእጅጉ እንደሚጠቅማቸው እንተማመናለን። ይሖዋ ከእሱ ጋር ያለንን ወዳጅነት ለማጠናከር ላደረገልን ለእነዚህ ዝግጅቶች ከልብ እናመሰግነዋለን።—መዝሙር 119:97
ዘፍጥረት 3:1 ላይ “እባብ” ለሚለው ቃል የተዘጋጀው ማመሣከሪያ ወደ ራእይ 20:2 በመውሰድ ‘የጥንቱን እባብ’ ማንነት ለማወቅ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ተመልከት