በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በራማፖ ዋናው ግንባታ ከመጀመሩ በፊት መሬቱን ለማዘጋጀት ከተከናወኑት ብዙ ሥራዎች አንዱ ጫካውን መመንጠር ነው

ኅዳር 8, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የዋናው መሥሪያ ቤት ፕሮጀክት በራማፖ

በራማፖ ትላልቅ የግንባታ ሥራዎች ለመጀመር የሚያስችል ፈቃድ አገኘን

በራማፖ ትላልቅ የግንባታ ሥራዎች ለመጀመር የሚያስችል ፈቃድ አገኘን

ኅዳር 6, 2024 የራማፖ ከተማ ፕላን ቦርድ የፕሮጀክታችንን የግንባታ ንድፍ አጽድቆልናል። ይህ ፈቃድ መገኘቱ፣ በቦታው ላይ ዋና ዋና የግንባታ እንቅስቃሴዎችን ለመጀመር የሚያስችለን ትልቅ እመርታ ነው።

ወደፊት በራማፖ የሚዲያ ሥራዎች በሚከናወኑበት ማዕከል ውስጥ ሊገነቡ የታቀዱት የቢሮ ሕንፃዎች ንድፍ

የከተማ ፕላን ቦርዱ ሰኔ 2023 በፕሮጀክቱ ልናከናውን ካሰብነው ግንባታ ለተወሰኑት ፈቃድ መስጠቱ ይታወሳል። ከዚህ በፊት የተገኙት ፈቃዶች፣ ቦታውን እንደ መመንጠር የመሰሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለማከናወን አስችለውናል። ሆኖም አሁን የተገኘው ፈቃድ፣ ዋናውን መግቢያ ለመሥራትና የአካባቢውን ዓለት በድማሚት በመፈርከስ ለመሠረት ግንባታ ለማዘጋጀት ያስችለናል። በተጨማሪም መሬት ቆፍሮ የውኃ መተላለፊያ ቱቦዎች እንደ መቅበር ዓይነት አስፈላጊ ሥራዎች ይጀመራሉ።

በግንባታ ፕሮጀክት ኮሚቴ ውስጥ የሚያገለግለው ወንድም ኬቨን ፔጅ እንዲህ ብሏል፦ “ይህን ፈቃድ በማግኘታችን በጣም ተደስተናል! በእያንዳንዱ ሂደት ይሖዋ ትዕግሥታችንንና ትጋታችንን እንደባረከልን ተመልክተናል። ለዚህ ትልቅ እመርታ እናመሰግነዋለን፤ ይህን የፕሮጀክቱ ክፍል መባረኩን እንዲቀጥልም እንጸልያለን።”

ፕሮጀክቱ እዚህ ደረጃ ላይ በመድረሱ መላው የወንድማማች ማኅበር ተደስቷል! ይሖዋ ፕሮጀክቱንም ሆነ በሥራው ላይ የሚሳተፉትን ሁሉ አብዝቶ ይባርክ ዘንድ እንጸልያለን።​—ሐጌ 1:14