ግንቦት 8, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና
በኬንያና በታንዛንያ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከተለ
በሚያዝያ 2024 በኬንያ እና በታንዛንያ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። በኬንያ ከ185,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን 200 ገደማ የሚሆኑ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአጎራባቿ በታንዛንያ 200,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ከመኖሪያቸው እንደተፈናቀሉና ወደ 200 የሚጠጉ ደግሞ ሕይወታቸውን እንዳጡ ይገመታል። በመጪዎቹ ሳምንታትም ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ኃይለኛ ዝናብ እንደሚጥል ይጠበቃል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
የሚያሳዝነው አንዲት እህትና ሴት ልጇ ሕይወታቸውን አጥተዋል
59 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
14 ቤቶች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል
3 የመሰብሰቢያ አዳራሾች እና ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች የሚካሄዱበት 1 ሕንፃ ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ ሽማግሌዎች በጎርፉ ለተጎዱት መንፈሳዊ ድጋፍ እየሰጡ ነው
በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንጸልያለን። የምንኖረው አስጨናቂ በሆነ ዘመን ቢሆንም በቅርቡ ‘ምንም ነገር የማንፈራበትና የሚያሸብረን ነገር የማይኖርበት’ ጊዜ እንደሚመጣ እንተማመናለን።—ኢሳይያስ 54:14