በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 20, 2020
ዓለም አቀፋዊ ዜና

በኮቪድ-19 የተነሳ ኤሌክትሮኒክ መዋጮ ማድረግ

በኮቪድ-19 የተነሳ ኤሌክትሮኒክ መዋጮ ማድረግ

በበርካታ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች በዚህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የተነሳ መንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸውን የሚያከናውኑበት መንገድ ተቀይሯል። ብዙዎቹ ወንድሞቻችን በአካል ወደ ስብሰባ አዳራሽ ከመሄድ ይልቅ ስብሰባ የሚያደርጉት የቪዲዮ ኮንፈረንስ ፕሮግራሞችን ተጠቅመው ነው። በዚህም ምክንያት ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ ድጋፍ የሚያደርጉበትን መንገድ በመቀየር በኢንተርኔት አማካኝነት መዋጮ ማድረግ ጀምረዋል።

ከ112 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ዴቢት ወይም ክሬዲት ካርድ በመጠቀም በ​donate.pr418.com አማካኝነት ኤሌክትሮኒክ መዋጮ ያደርጋሉ።

አብዛኞቹ አስፋፊዎች በስብሰባ አዳራሻቸው መዋጮ ማድረግ አይችሉም፤ በዚህም የተነሳ አንዳንድ አስፋፊዎች donate.pr418.com ላይ “በየወሩ መዋጮ አድርግ” የሚለውን ገጽታ በመጠቀም በቋሚነት መዋጮ ያደርጋሉ። በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩት እህት ሱዛን ኮኸን የተባሉ የ74 ዓመት አስፋፊ ይህን ገጽታ ይጠቀማሉ። እንዲህ ብለዋል፦ “በጣም ቀላል ነው፤ እኔ ይህን ገጽታ መጠቀም ከቻልኩ ማንም ሰው አያቅተውም። በዚህ መንገድ ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ መዋጮ ማድረግ በመቻሌ በጣም ደስተኛ ነኝ።”

በብራዚል የሚኖረው ወንድም ኤድዋርዶ ፓይቫ donate.pr418.com​ን የሚመለከተው በአካል መዋጮ ማድረግ ሳይቻል ሲቀር መዋጮ ለማድረግ እንደሚያስችል አማራጭ ዘዴ አድርጎ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “አሁን ግን ድንገተኛ ሁኔታ በሚያጋጥምበት ጊዜም ጭምር ዓለም አቀፉን ሥራ ለመደገፍ የሚያስችል ግሩም ዘዴ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ። በዚህ መንገድ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት አመስጋኝነታችንን እና ፍቅራችንን መግለጽ እንችላለን።”

በዎርዊክ፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የገንዘብ ያዥ ቢሮ የበላይ ተመልካች ሆኖ የሚያገለግለው ወንድም ጋይዩስ ግሎከንቲን እንዲህ ብሏል፦ “ወንድሞች ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመደገፍ ያላቸውን ፍላጎት ማየት እምነት የሚያጠናክር ነው። እነዚህን መዋጮዎች አቅልለን አንመለከታቸውም። በመዋጮ የተገኘውን ገንዘብ በአግባቡ መጠቀም ስለምንፈልግ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎቻችንን በየጊዜው በመገምገም ወጪ ለመቀነስ እንሞክራለን። አንዳንዶች መዋጮ የሚያደርጉትን የገንዘብ መጠን ለመቀነስ ቢገደዱም የይሖዋን ድርጅት ለመደገፍ ያላቸው ቁርጠኝነት ግን አልቀነሰም።”—2 ቆሮንቶስ 9:7