በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ቤርል የተባለው አውሎ ነፋስ ሐምሌ 5, 2024 በሜክሲኮው ዩካታን ባሕረ ገብ መሬት ሲያልፍ የሚያሳይ የሳተላይት ምስል

ሐምሌ 12, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ቤርል የተባለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ የሚሊዮኖችን ሕይወት አቃወሰ

ቤርል የተባለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ የሚሊዮኖችን ሕይወት አቃወሰ

ሰኔ 30, 2024 ቤርል የተባለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በዌስት ኢንዲስ የምትገኘውን የማርቲኒክ ደሴት ደቡባዊ ክፍል መትቷል፤ በወቅቱ አውሎ ነፋሱ እርከን 3 ደረጃ ተሰጥቶት ነበር። በማግስቱ ግን ይበልጥ እየተጠናከረ በመሄዱ እርከን 4 ደረጃ የተሰጠው ሲሆን በዊንድወድ ደሴቶች (ባርባዶስ፣ ግሬኔዳ እንዲሁም ሴንት ቪንሰንት እና ግሬናዲንዝ) ላይ ጉዳት አድርሷል። ቤርል በቀጣዩ ቀን ቬኔዙዌላን ሲመታ ይበልጥ አይሎ እርከን 5 ደርሶ ነበር። ከዚያም በጃማይካ ደቡባዊ ወደብ አለፈ። ይህ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ሐምሌ 5 ደግሞ ዩካታን በተባለው የሜክሲኮ ባሕረ ገብ መሬት፣ ቀጥሎም በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ጉዳት አድርሷል።

በሰዓት እስከ 270 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት የሚጓዘውና ዶፍ ዝናብ የቀላቀለው ይህ አውሎ ነፋስ፣ በመኖሪያ ቤቶችና በንግድ ቦታዎች እንዲሁም በመሠረተ ልማት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል፣ ውኃ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት አልቻሉም። ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከ30 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

ማርቲኒክ (ዌስት ኢንዲስ)

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 6 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 1 ቤት ወድሟል

  • 1 ቤት ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 1 ቤት ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

  • አንድም የስብሰባ አዳራሽ ጉዳት አልደረሰበትም

በዊንድወድ ደሴቶች ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ

ዊንድወድ ደሴቶች

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 7 አስፋፊዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 67 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 39 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 31 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ወድሟል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 4 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

ቬኔዙዌላ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 30 አስፋፊዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል

  • 12 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 9 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

ጃማይካ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 18 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 24 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 75 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 19 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

ሜክሲኮ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 320 አስፋፊዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገው ነበር፤ አሁን ወደ መኖሪያቸው ተመልሰዋል

  • 11 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • አንድም የስብሰባ አዳራሽ ጉዳት አልደረሰበትም

ዩናይትድ ስቴትስ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 6 አስፋፊዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 242 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 4 ቤቶች ወድመዋል

  • 33 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 471 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • አንድም የስብሰባ አዳራሽ ጉዳት አልደረሰበትም

የእርዳታ እንቅስቃሴ

የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩት መንፈሳዊና ቁሳዊ እርዳታ እያደረጉ ነው። በተጨማሪም የእርዳታ ሥራውን ለማደራጀት ስድስት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል።

ይሖዋ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በእሱ የሚታመኑትን ሁሉ ማጽናናቱን እንዲቀጥል ጸሎታችን ነው።​—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4