በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ ከላይ፦ በፋኤንዛ፣ ጣሊያን በጎርፍ የተጥለቀለቀ የስብሰባ አዳራሽ፤ በስተ ግራ ከታች፦ በጉኾዋዜ፣ ፖላንድ በጎርፍ የተጥለቀለቀ የስብሰባ አዳራሽ፤ በስተ ቀኝ፦ በኩዳልቢ፣ ሩማንያ ጎርፉ ጉዳት ያደረሰበት የአንዲት እህት ቤት

ጥቅምት 2, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ቦሪስ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በመካከለኛው አውሮፓ አንዳንድ ክፍሎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከተለ

ቦሪስ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በመካከለኛው አውሮፓ አንዳንድ ክፍሎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከተለ

ከመስከረም 11, 2024 ጀምሮ፣ ቦሪስ የተባለው ኃይለኛ ወጀብ በአንዳንድ የመካከለኛው አውሮፓ ክፍሎች ዶፍ ዝናብና ኃይለኛ ነፋስ አስከትሏል። ይህ ወጀብ መስከረም 12 ደቡባዊ ፖላንድን ሲመታ በአንዳንድ ቦታዎች ከ24 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ 20 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ዝናብ ጥሏል፤ በዚህም የተነሳ በርካታ ከተሞች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል። በተጨማሪም ረዘም ላለ ጊዜ የቀጠለው ኃይለኛ ዝናብ በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ጉዳት በማድረሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል። በቀጣዩ ቀን ማለትም መስከረም 13 ቦሪስ በቼክ ሪፑብሊክ ሰሜናዊ ክፍሎች ላይ ከ50 ሴንቲ ሜትር የሚበልጥ ዝናብ አወረደ፤ ይህም በመኖሪያ ቤቶች፣ በመንገዶችና በድልድዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።

መስከረም 14 ደግሞ በሩማንያ 25 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ዝናብ በመጣሉ በአገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ መንደሮች በጎርፍ ተጥለቀለቁ። ወደ 5,000 የሚጠጉ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ እንዲሁም በጋላቲ ግዛት ሁለት ግድቦች ተደርምሰዋል። መስከረም 18 ቦሪስ ሰሜናዊ ጣሊያን ደረሰ። በብዙ ቦታዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ብቻ ወደ 30 ሴንቲ ሜትር የሚጠጋ ዝናብ ጣለ፤ በዚህም የተነሳ ወንዞች ሞልተው አካባቢውን አጥለቀለቁት።

ይህ ኃይለኛ ወጀብ በአራቱም አገራት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከመኖሪያቸው ያፈናቀለ ሲሆን 19 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

ቼክ ሪፑብሊክ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 79 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 12 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

ጣሊያን

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 63 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 7 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 21 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 4 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

ፖላንድ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 87 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 61 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 85 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 8 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

ሩማንያ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 1 አስፋፊ ከመኖሪያው ተፈናቅሏል

  • 2 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 5 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • ጉዳት የደረሰበት ወይም የፈረሰ የስብሰባ አዳራሽ የለም

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የእርዳታ ሥራውን እንዲያስተባብሩ 6 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የአካባቢው ሽማግሌዎች በጎርፉ ጉዳት ለደረሰባቸው መንፈሳዊ እርዳታና ሌሎች አስፈላጊ እገዛዎችን እያደረጉ ነው

ወንድሞችና እህቶች በእርዳታ ሥራው ሲካፈሉ፦ ጣሊያን (በስተ ግራ)፣ ፖላንድ (ከላይ በስተ ቀኝ)፣ እና ሩማንያ (ከታች በስተ ቀኝ)

በዚህ መጠነ ሰፊ የጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው መጸለያችንን እንቀጥላለን፤ አፍቃሪው አባታችን ይሖዋ የሚያስፈልጋቸውን መጽናኛና ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው እንተማመናለን።​—ኢሳይያስ 40:11