ኅዳር 22, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና
ቮይስ አሲስታንት ላይ ተጨማሪ የJW.ORG ትእዛዞች ተካተቱ
ከ2019 ወዲህ አማዞን አሌክሳ ወይም ጉግል አሲስታንት ያላቸው መሣሪያዎች ከjw.org ላይ የተወሰኑ ፋይሎችን ማጫወት እንደጀመሩ ይታወቃል። አሁን ደግሞ ሌሎች የስብሰባና የአገልግሎት ሚዲያዎችንም ማጫወት እንዲቻል ተጨማሪ የድምፅ ትእዛዞች ተካትተዋል። በእርግጥ ጉግል ከሰኔ 2023 በኋላ ይህን አገልግሎት መስጠት እንደሚያቆም አሳውቋል። እስከዚያው ድረስ ግን በጉግል አሲስታንት አማካኝነት ይህን አገልግሎት ማግኘት ይቻላል። አማዞን አሌክሳ የሚሰጠው አገልግሎት በዚሁ ይቀጥላል።
በአሁኑ ወቅት ተጠቃሚዎች ስልካቸውን በድምፅ በማዘዝ የሚከተሉትን ፕሮግራሞች ማጫወት ይችላሉ፦ በክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ላይ ያለውን ሳምንታዊ ፕሮግራምና ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ በተባለው ብሮሹር ላይ ያሉትን ምዕራፎች። ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲዘጋጁ ደግሞ ተጠቃሚዎች ለዘላለም በደስታ ኑር! ከተባለው መጽሐፍ ላይ የሚፈልጉትን ምዕራፍ እንዲያጫውትላቸው በድምፅ ማዘዝ ይችላሉ።
በስብሰባዎቻችን ላይ የሚዘመሩ መዝሙሮችን እንዲሁም በድምፅ ወይም በመሣሪያ የተቀነባበሩ መዝሙሮችንም በድምፅ ትእዛዝ መክፈት ተችሏል። ወቅታዊ የበላይ አካል ሪፖርቶችንም እንዲሁ።
በእያንዳንዱ ቮይስ አሲስታንት ላይ ይህን አገልግሎት እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ለማወቅ “Use the JW.ORG Skill for Amazon Alexa” ወይም “Use the JW.ORG Action for Google Assistant” የሚሉትን ርዕሶች ተመልከት።
ቮይስ አሲስታንት የሌላቸው ብዙዎቹ ስልኮች፣ ታብሌቶችና ኮምፒውተሮችም ይህን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፤ ማድረግ የሚጠበቅባቸው አሌክሳ አፕሊኬሽንን መጫን ነው።
እነዚህ አዳዲስ ገጽታዎች በተለይ ለዓይነ ስውራን ወይም ማየት ለሚቸገሩ ሰዎች በጣም ጠቃሚ ናቸው። አንተ እንዲህ ዓይነት ወዳጅ ካለህ መሣሪያው ላይ ቮይስ አሲስታንት በማስጀመር ወይም አፕሊኬሽን በመጫን እንዲሁም አጠቃቀሙን በማሳየት ልታግዘው ትችል ይሆን?