በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 17, 2021
ዓለም አቀፋዊ ዜና

አዲስ ዓለም ትርጉም በታጂኪ ቋንቋ ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም በታጂኪ ቋንቋ ወጣ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ማርክ ሳንደርሰን ሰኔ 13, 2021 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በታጂኪ ቋንቋ መውጣቱን አበሰረ። መጽሐፍ ቅዱሱ በዲጂታል ፎርማት መውጣቱ የተገለጸው አስቀድሞ በተቀረጸ ንግግር አማካኝነት ነው።

አጭር መረጃ

  • 14 ሚሊዮን ያህል ሰዎች የታጂኪ ቋንቋን እንደሚናገሩ ይገመታል፤ ከእነዚህ መካከል 5 ሚሊዮን ገደማ ያህሉ የሚኖሩት በታጂኪስታን ነው

  • በተለያዩ አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ተርጓሚዎች በሥራው የተካፈሉ ሲሆን ሥራውን ለማጠናቀቅ 4 ዓመት ገደማ ወስዶባቸዋል

አንዱ ተርጓሚ እንዲህ ብሏል፦ “አዲስ ዓለም ትርጉም በታጂኪ ቋንቋ በመውጣቱ አንባቢዎች መልእክቱን በቀላሉ መረዳትና በሥራ ላይ ማዋል ይችላሉ። ይህ ትርጉም፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ወደሆነው ወደ ይሖዋ ይበልጥ ለመቅረብ ሁሉንም እንደሚረዳቸው አልጠራጠርም።”—ያዕቆብ 4:8