ጥቅምት 4, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና
ኢያን የተባለው አውሎ ነፋስ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ
ኢያን የተባለው ኃይለኛ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ መስከረም 27, 2022 በኩባ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፤ በማግሥቱ ደግሞ በደቡባዊ ምዕራብ ፍሎሪዳ ላይ በ4ኛ እርከን የሚመደብ ኃይለኛ ዝናብ አስከትሏል። ዩናይትድ ስቴትስ ካጋጠሟት ኃይለኛ አውሎ ነፋሶች አንዱ የሆነው ኢየን በሰዓት 240 ኪሎ ሜትር ይጓዝ ነበር። ዝናብ የቀላቀለው አውሎ ነፋስ ዩናይትድ ስቴትስን አቋርጦ አትላንቲክ ውቅያኖስ እስኪደርስ ድረስ በርካታ ሰፈሮችን አውድሟል፣ በብዙ ቦታዎች የኃይል መቆራረጥ አስከትሏል፣ መሠረተ ልማቶችን አውድሟል እንዲሁም በጣም ሰፊ አካባቢዎችን በጎርፍ አጥለቅልቋል። በኋላ ላይ ደግሞ ደቡባዊ ካሮላይናን መትቷል።
በዚህ አውዳሚ አውሎ ነፋስ የተነሳ በፍሎሪዳ የሚኖሩ ከ12,000 የሚበልጡ አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ተወካዮች በአካባቢው ካሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር ሆነው ጉዳት የደረሰባቸውን መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላት እየተረባረቡ ነው።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ኩባ
የሚያሳዝነው 1 ወንድማችን ሕይወቱን አጥቷል
2 ወንድሞች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
300 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
491 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
63 ቤቶች ወድመዋል
40 የስብሰባ ቦታዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 የትላልቅ ስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል
3 የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
ፍሎሪዳ
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል በአደጋው ማንም አልሞተም
2 አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
5,874 አስፋፊዎች በአሁኑ ወቅት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
1,559 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
367 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
47 ቤቶች ወድመዋል
329 ቤቶች መለስተኛ ጥገና ስለተደረገላቸው መኖሪያ መሆን ችለዋል
71 ቤቶች ጥገና ተደርጎላቸዋል
38 ለቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴ የሚውሉ ሕንፃዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
1 የትላልቅ ስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
ደቡባዊ ካሮላይና
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል በአደጋው ጉዳት የደረሰበት ወይም ሕይወቱን ያጣ የለም
35 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
13 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች እረኝነት እያደረጉ እንዲሁም አስፈላጊውን እርዳታ እየሰጡ ነው
በፍሎሪዳ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ወንድሞችና እህቶችን ለመርዳት 14 ጊዜያዊ የእርዳታ ማዕከላት ተዘጋጅተዋል
በፍሎሪዳና በኩባ የእርዳታ ሥራውን የሚያስተባብሩ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል
ሁሉም የእርዳታ እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች በተከተለ መልኩ ነው
ወንድሞቻችን አደገኛ ሁኔታ ባጋጠማቸው ወቅት የእምነት ባልንጀሮቻቸውን እገዛ በማግኘታቸው “በይሖዋ የሚታመን ሰው . . . ታማኝ ፍቅሩ ይከበዋል” የሚለውን የመዝሙራዊውን ሐሳብ እውነተኝነት በሕይወታቸው ተመልክተዋል።—መዝሙር 32:10