በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በጓቴማላ (በስተግራ) እና በኮስታ ሪካ (በስተቀኝ) የተከሰተው ጎርፍ

ኅዳር 20, 2020
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ኤታ የተባለው አውሎ ነፋስ ማዕከላዊ አሜሪካን፣ ኬይማን ደሴቶችን፣ ባሃማስን፣ ጃማይካን፣ ሜክሲኮንና ዩናይትድ ስቴትስን መታ

ኤታ የተባለው አውሎ ነፋስ ማዕከላዊ አሜሪካን፣ ኬይማን ደሴቶችን፣ ባሃማስን፣ ጃማይካን፣ ሜክሲኮንና ዩናይትድ ስቴትስን መታ

ቦታ

ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ባሃማስ፣ ግራንድ ኬይማን ደሴት፣ ጃማይካ፣ ሜክሲኮና ደቡብ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ

የደረሰው አደጋ

  • በእርከን 4 የሚመደበው ኤታ የተባለው አውሎ ነፋስ ኅዳር 3, 2020 ላይ ፖርቶ ካቤዛስ፣ ኒካራጓን ከመታ በኋላ ወደ ሌሎች የማዕከላዊ አሜሪካ ክፍሎች በመጓዝ ከባድ ጉዳት አስከትሏል

  • የሚያሳዝነው በታባስኮ፣ ሜክሲኮ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክር ባልና ሚስት የልጅ ልጅ የሆነ አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጅ በጎርፍ ተወስዶ ሞቷል

  • ኤታ የተባለው አውሎ ነፋስ ኃይሉ ከቀነሰ በኋላም በግራንድ ኬይማን ደሴት፣ በባሃማስና በጃማይካ ላይ ጉዳት አድርሷል። በኋላም ወደ ሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ በመጓዝ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ጉዳት አስከትሏል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ኮስታ ሪካ

    • 108 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

    • 7 አስፋፊዎች ንብረታቸውን ሁሉ አጥተዋል

  • ጓቴማላ

    • መጀመሪያ ላይ 163 አስፋፊዎች ተፈናቅለው ነበር፤ ከእነዚያ መካከል 85ቱ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል

    • 3 ቤተሰቦች ንብረታቸውን ሁሉ አጥተዋል

    • በተጨማሪም አንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ ሦስት አስፋፊዎች የአደጋ ጊዜ እርዳታ የሚሰጡ ሰዎች መጥተው እስኪረዷቸው ድረስ ከመኖሪያቸው አንደኛ ፎቅ መውጣት አልቻሉም ነበር

  • ሆንዱራስ

    • መጀመሪያ ላይ 1,984 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ነበር፤ ቢያንስ 376ቱ ተመልሰዋል

  • ጃማይካ

    • 4 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • ሜክሲኮ

    • ቺያፓስ እና ታባስኮ በተባሉት ግዛቶች ውስጥ የሚኖሩ 1,618 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ነበር፤ 112ቱ ተመልሰዋል

  • ኒካራጓ

    • 238 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ነበር፤ 232ቱ ተመልሰዋል

  • ፓናማ

    • 27 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ነበር፤ 6ቱ ተመልሰዋል

  • ዩናይትድ ስቴትስ

    • 48 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ነበር፤ 27ቱ ተመልሰዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ባሃማስ

    • 1 ቤት ጉዳት ደርሶበታል

  • ኮስታ ሪካ

    • 3 ቤቶች ፈርሰዋል

    • 6 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • ጓቴማላ

    • 2 ቤቶች በመሬት መንሸራተት ምክንያት ፈርሰዋል

  • ሆንዱራስ

    • 7 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • ኒካራጓ

    • 73 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • ግራንድ ኬይማን ደሴት

    • 4 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

    • 1 የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

  • ጃማይካ

    • 50 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

    • 1 የስብሰባ አዳራሽ ጉዳት ደርሶበታል

  • ዩናይትድ ስቴትስ

    • 141 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

    • 9 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የማዕከላዊ አሜሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ አስፈላጊውን የእርዳታ ሥራ እንዲያስተባብሩ በሜክሲኮ ሁለት በሆንዱራስ ደግሞ አንድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል። ጉዳት በደረሰባቸው ሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የተቋቋሙት የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በአውሎ ነፋሱ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ

  • በዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ክልል ውስጥ ያሉ ጉባኤዎችና ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የተቋቋሙት የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በእርዳታ ሥራው ድጋፍ እያደረጉ ነው

  • በእነዚህ አካባቢዎች በሙሉ ያሉት የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ቅዱስ ጽሑፋዊ ማበረታቻ እየሰጡ ይገኛሉ

  • አደጋ ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ያሉ ወንድሞችና እህቶች ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉት ሰዎች መጠለያና ምግብ አቅርበዋል

  • ሁሉም የእርዳታ ሥራዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ይህ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ከባድ ጉዳት ቢያስከትልም ወንድሞቻችን እርስ በርስ ሲደጋገፉ በማየታችን ተበረታተናል። አምላካችን ይሖዋ በዚህ ‘የመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ’ መሆኑን እንደሚያሳይ እንተማመናለን።—መዝሙር 9:9