ጥር 23, 2024 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 18, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና
ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “እምነት ላለው ሰው፣ ሁሉ ነገር ይቻላል”
ሚያዝያ 16, 2024 በሴቫስቶፖል የሚገኘው የናኪሞቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ማክሲም ዚንችዬንኮ ጥፋተኛ ነው በማለት የሁለት ዓመት የግዳጅ የጉልበት ሥራ በይኖበታል። ማረሚያ ተቋም ውስጥ እየኖረ በተመደበለት አካባቢ የሚሰጠውን ሥራ ማከናወን ይኖርበታል።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ፣ ማክሲምም ሆነ የእሱን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ ለሚያሳዩት ድፍረትና ጽናት ወሮታ እንደሚከፍላቸው እንተማመናለን።—ዕብራውያን 10:35, 36
የክሱ ሂደት
ግንቦት 17, 2023
በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ በመካፈል ተከሰሰ
ግንቦት 22, 2023
ቤቱ ተፈተሸ። በማክሲም እና በካሪና ላይ ምርመራ ተካሄደባቸው፤ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያ ጣቢያ እንዲገባ ተደረገ
ግንቦት 24, 2023
ከጊዜያዊ ማረፊያ ጣቢያ ወጥቶ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ
ሐምሌ 12, 2023
ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ