ግንቦት 9, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና
ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | በክራይሚያ ያሉ ቤተሰቦች በይሖዋ እርዳታ ጸንተዋል
ጥቅምት 6, 2022 በሴቫስቶፖል የሚገኘው የናኪሞቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ቭላድሚር ማላዲካ፣ በወንድም ቭላድሚር ሳካዳ እና በወንድም ዬቭጌኒ ዡኮቭ ላይ ብይን አስተላልፏል። እያንዳንዳቸው የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ወዲያውኑ ወህኒ ወርደዋል።
የክሱ ሂደት
ጥቅምት 1, 2020
የፊዴራል ደህንነት አባላት የወንድም ማላዲካ የወንድም ሳካዳ እና የወንድም ዡኮቭ ቤት ጨምሮ በሴቫስቶፖል የሚኖሩ ዘጠኝ የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦችን ቤቶች ፈተሹ። የወንድም ማላዲካ ቤት በተፈተሸበት ወቅት ፖሊሶቹ በአንድ ትንሽ ዕቃ ውስጥ ዱቄት ወተት አገኙ። ፖሊሶቹ ዱቄቱ “አደንዛዥ ዕፅ” እንደሚመስል በመናገር ወንድም ማላዲካን እና ባለቤቱን ናታሊያን ለምርመራ ወደ አእምሮ ሐኪም ቤት ላኳቸው። ናታሊያ በዚያው ዕለት ተለቀቀች። ወንድም ማላዲካ እንዲሁም ወንድም ሳካዳ እና ወንድም ዡኮቭ ግን ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ተወሰዱ። በቀጣዩ ቀን ወደ ማረፊያ ቤት ተላኩ
መጋቢት 23, 2021
ወንድም ሳካዳ ከማረፊያ ቤት ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ። የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ መሣሪያ እንዲያደርግ የተገደደ ከመሆኑም ሌላ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም፣ ስልክ እንዳይደውል እንዲሁም በክሱ ውስጥ ከተካተቱት ሌሎች ወንድሞች ጋር እንዳይነጋገር ተከለከለ
መጋቢት 30, 2021
ወንድም ማላዲካ ከማረፊያ ቤት ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ግንቦት 17, 2021
ወንድም ዡኮቭ ከሰባት ወር በላይ በማረፊያ ቤት ከቆየ በኋላ ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
መስከረም 30, 2021
ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ እነዚህን ወንድሞች ጨምሮ በክራይሚያ ስደት እየደረሰባቸው ያሉትን ሁሉ ልባቸውን እንደሚያጸናላቸው እርግጠኞች ነን።—1 ተሰሎንቄ 3:12, 13