በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ ወንድም ዩሪ ጌራሽቼንኮ እና ባለቤቱ ኢሪና። በስተ ቀኝ፦ ወንድም ሰርጌ ማርፌኖቪች እና ባለቤቱ ማሪና

ጥር 9, 2024 | የታደሰው፦ ጥቅምት 7, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ይሖዋን የሙጥኝ ብለው ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ይሖዋን የሙጥኝ ብለው ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል

ጥቅምት 3, 2024 የክራይሚያ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንድም ዩሪ ጌራሽቼንኮ እና በወንድም ሰርጌ ፓርፌኖቪች ላይ ቀደም ሲል የተላለፈውን ፍርድ ቀይሮታል። ተላልፎባቸው የነበረው የስድስት ዓመት የገደብ እስራት በስድስት ዓመት እስራት እንዲለወጥ በይኗል። ከፍርድ ቤት ወደ ወህኒ ተወስደዋል።

ሐምሌ 1, 2024 በክራይሚያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የክራስኖግቫርዴስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ዩሪ ጌራሽቼንኮ እና ወንድም ሰርጌ ፓርፌኖቪች ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሁለቱም የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል፤ አሁን ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ እንደ ወንድም ዩሪ እና ሰርጌ ያሉ ንጹሕ አቋማቸውን የሚጠብቁ ወንድሞቻችንን ‘በክንፎቹ ጥላ በመሰወር’ መርዳቱን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።​—መዝሙር 17:7, 8

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 19, 2022

    በሰርጌ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  2. መስከረም 28, 2022

    የፌዴራል ደህንነት ሠራተኞች ከፈተሿቸው ስምንት ቤቶች መካከል አንዱ የሰርጌ ቤት ነበር፤ በኋላም በጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ እንዲቆይ ተደረገ

  3. መስከረም 30, 2022

    ሰርጌ ማረፊያ ቤት ገባ

  4. ኅዳር 15, 2022

    ሰርጌ ከማረፊያ ቤት ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ

  5. መጋቢት 22, 2023

    በዩሪ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተበት። ከታሰረ በኋላ ምርመራ ተካሂዶበት ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ተወሰደ

  6. መጋቢት 24, 2023

    ዩሪ ከጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ወጥቶ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ

  7. ሐምሌ 12, 2023

    ሰርጌ እና ዩሪ ከቁም እስር ነፃ ተለቀው የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው

  8. ሐምሌ 28, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። አቃቤ ሕጉ ሰርጌ እና ዩሪ “በወንጀል እንቅስቃሴዎች መካፈላቸውንና ምሥክሮችን ማስፈራራታቸውን” ቀጥለዋል የሚል ክስ አቀረበባቸው። በቂ ማስረጃ ባይቀርብባቸውም ዳኛው ሁለቱም ድጋሚ በቁም እስር እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላለፈ