መስከረም 27, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 22, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና
ወቅታዊ መረጃ—የጥፋተኝነት ብይን ተቀለበሰ | በይሖዋ እርዳታ አሉታዊ ስሜቶችን ማሸነፍ
መጋቢት 21, 2024 የክራይሚያ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ታራስ ኩዝዮ እና ባለቤቱ እህት ዳርያ ኩዝዮ እንዲሁም በወንድም ሰርጌ ልዩሊን እና በወንድም ፕዮተር ዢልትሶቭ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ብይን ሽሯል። ወንድሞች ወዲያውኑ ከእስር ተለቀዋል። ክሳቸው በድጋሚ እንዲታይ በክራይሚያ ሪፑብሊክ ወደሚገኘው የያልታ ከተማ ፍርድ ቤት ተመልሷል።
የካቲት 27, 2023 በክራይሚያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የያልታ ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ታራስ ኩዝዮ እና ባለቤቱ እህት ዳርያ ኩዝዮ እንዲሁም ወንድም ሰርጌ ልዩሊን እና ወንድም ፕዮተር ዢልትሶቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዳርያ የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም። ታራስ የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶበታል። ሰርጌ እና ፕዮተር ደግሞ እያንዳንዳቸው የስድስት ዓመት ከአንድ ወር እስራት ተበይኖባቸዋል። ሦስቱም ወንድሞች ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወደ ወህኒ ቤት ተወስደዋል።
የክሱ ሂደት
መጋቢት 4, 2021
ታራስ ‘ለጽንፈኛ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል’ በሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተበት
መጋቢት 11, 2021
የእነ ታራስንና የእነ ሰርጌን ቤት ጨምሮ ዘጠኝ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። ታራስ ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ
መጋቢት 12, 2021
ታራስ ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ፤ ሆኖም ከቤተሰቡ ጋር እንዲኖር አልተፈቀደለትም
ሐምሌ 29, 2021
በዳሪያ፣ በፕዮተርና በሰርጌ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ። ፕዮተር ማረፊያ ቤት እንዲገባ ተደረገ
ሐምሌ 30, 2021
የሁሉም ክስ በአንድ መዝገብ ተካተተ። ፕዮተር ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ
ነሐሴ 11, 2021
ሰርጌ በቁጥጥር ሥር ውሎ 800 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቆ ወደሚገኝ ማረፊያ ቤት ተወሰደ። አሥራ ስድስት ሰዓት በፈጀው ጉዞ ላይ እጆቹ ከጭንቅላቱ በላይ ካለ ዘንግ ጋር ታስረው እንዲሁም እግሮቹ ከወንበሩ ጋር ታስረው ነበር
መጋቢት 1, 2022
ሰርጌ ከማረፊያ ቤት ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ
ሚያዝያ 4, 2022
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ሐምሌ 11, 2022
ፕዮተር፣ ሰርጌና ታራስ ከቁም እስር ነፃ ተደረጉ፤ የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው
አጭር መግለጫ
በእስር ቤት፣ በማረፊያ ቤት ወይም በቁም እስር ላይ የሚገኙ ታማኝ ክርስቲያኖች ‘መፈናፈኛ እንዳጡ’ ይሰማቸው ይሆናል፤ ሆኖም ይሖዋ ለስሙ ሲሉ የሚሰደዱ ክርስቲያኖችን ፈጽሞ አይተዋቸውም።—2 ቆሮንቶስ 4:8, 9