በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ዱቦቬንኮ እና አሌክሳንደር ሊትቪንዩክ

ታኅሣሥ 8, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ወንድም ዱቦቬንኮ እና ሊትቪንዩክ የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

ወንድም ዱቦቬንኮ እና ሊትቪንዩክ የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

ኅዳር 30, 2022 በክራይሚያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የአርምያንስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም አሌክሳንደር ዱቦቬንኮ እና አሌክሳንደር ሊትቪንዩክ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሁለቱም ወንድሞች የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው ወዲያውኑ ወደ ወህኒ ቤት ተወስደዋል።

አጭር መግለጫ

በፈተና ውስጥ ስናልፍ የትም እንሁን የት ይሖዋ ከጎናችን እንደሆነ ማወቃችን በጣም ያጽናናል።—መዝሙር 139:7-12

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 2, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው። ሁለቱም ወንድሞች፣ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ ለማራመድ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ፕሮግራም ተጠቅማችኋል ተብለው ተከሰሱ

  2. ነሐሴ 5, 2021

    የሁለቱን ወንድሞች ጨምሮ በስምንት የይሖዋ ምሥክሮች ቤተሰቦች መኖሪያ ላይ ፍተሻ ተካሄደ። ወንድም ሊትቪንዩክ ተይዞ ወደ ጣቢያ ተወሰደ

  3. ነሐሴ 6, 2021

    ወንድም ሊትቪንዩክ ከጣቢያ ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ

  4. ነሐሴ 9, 2021

    ፖሊሶች የአሌክሳንደር ዱቦቬንኮን መኖሪያ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ፈተሹ። አሌክሳንደር ምርመራ ከተደረገበት በኋላ የቁም እስረኛ ተደረገ

  5. ነሐሴ 11, 2021

    ወንድም ሊትቪንዩክ፣ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብረሃል በሚል በይፋ ክስ ተመሠረተበት

  6. የካቲት 8, 2022

    ወንድም ዱቦቬንኮ፣ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አስተባብረሃል በሚል በይፋ ክስ ተመሠረተበት

  7. ሚያዝያ 29, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ። ወንድም ሊትቪንዩክ የቁም እስር ላይ በነበረበት ወቅት ሐኪም ጋር ለመሄድ ያቀረበውን ጥያቄ ዳኛው ውድቅ አደረጉ

  8. መስከረም 8, 2022

    ሁለቱም ወንድሞች ከጠዋቱ 1:00 እስከ ምሽቱ 1:00 ከቤታቸው ውጭ መንቀሳቀስ ተፈቀደላቸው

  9. ኅዳር 30, 2022

    ሁለቱም ወንድሞች የስድስት ዓመት እስራት ተፈረደባቸው

a b አስተያየታቸውን ማግኘት የቻልነው ከመታሰራቸው በፊት ነው።