በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የማቴዎስ መጽሐፍ በኩርድ ኩርማንጂኛ እና በኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) በመውጣቱ በመላው አውሮፓ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ወንድሞችና እህቶች ተደስተዋል

ሐምሌ 11, 2023
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የማቴዎስ መጽሐፍ በኩርድ ኩርማንጂኛ እና በኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) ወጣ

የማቴዎስ መጽሐፍ በኩርድ ኩርማንጂኛ እና በኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) ወጣ

ሐምሌ 2, 2023 መጽሐፍ ቅዱስ—የማቴዎስ ወንጌል በሁለት የኩርድ ቋንቋዎች በሁለት የተለያዩ ፕሮግራሞች ላይ ወጣ። ጀርመን ውስጥ በኩርድ ኩርማንጂኛ፣ ጆርጂያ ውስጥ ደግሞ በኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) መጽሐፉ መውጣቱ ተበስሯል። ወደ 750 የሚጠጉ ሰዎች በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ ተገኝተዋል።

የኩርድ ኩርማንጂኛ

የማዕከላዊ አውሮፓ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ደርክ ቹፔክ፣ በኩርድ ኩርማንጂኛ የተዘጋጀውን የማቴዎስ ወንጌል መውጣት አብስሯል፤ መጽሐፉ መውጣቱ ይፋ የተደረገው በዜልተርስ፣ ጀርመን በሚገኘው የማዕከላዊ አውሮፓ ቅርንጫፍ ቢሮ በተካሄደ ልዩ ፕሮግራም ላይ ነው። በፕሮግራሙ ላይ በአካል ለተገኙት የታተመው ቅጂ ተሰጥቷቸዋል። በዚያው ዕለት የመጽሐፉ ኤሌክትሮኒክ ቅጂም ተለቅቋል።

የኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ)

የጆርጂያ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ሌቫኒ ኮፓሊያኒ በተብሊሲ፣ ጆርጂያ በተካሄደ ፕሮግራም ላይ በኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) የተዘጋጀው የማቴዎስ ወንጌል መውጣቱን አብስሯል። አፓራን፣ አርማቪር እና የረቫን በተባሉት የአርሜንያ ከተሞች የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች ፕሮግራሙን በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ተከታትለዋል። በፕሮግራሙ ላይ በአካል ለተገኙት የታተመው ቅጂ ተሰጥቷቸዋል። በዚያው ዕለት የመጽሐፉ ኤሌክትሮኒክ ቅጂም ተለቅቋል።

ኩርድ ኩርማንጂኛ እና ኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) ተቀራራቢ ቋንቋዎች ቢሆኑም ሰዋስዋቸውና የዓረፍተ ነገር አወቃቀራቸው የተለያየ ነው። በተጨማሪም አንዳንድ ቃላት በተመሳሳይ ሆሄያት ቢጻፉም የተለያየ ትርጉም ሊኖራቸው ይችላል። በመሆኑም ሁለቱም የትርጉም ቡድኖች የማቴዎስ ወንጌልን በየቋንቋቸው የተረጎሙት እየተመካከሩ ነው። አንድ ተርጓሚ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ማግኘታቸው የሚያስገኘውን ጥቅም ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “እውነትን ለተጠሙ ለብዙዎቹ ኩርዶች ይህ አዲስ ትርጉም ንጹሕ ውኃ የመጠጣት ያህል ጥም የሚቆርጥ ይሆንላቸዋል።”

በዚህ ትርጉም አማካኝነት ይሖዋ ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን ማርካት የሚችሉበት መንገድ ከፍቶላቸዋል፤ በመሆኑም ኩርድ ኩርማንጂኛ እና ኩርድ ኩርማንጂኛ (የኮውከሰስ) ተናጋሪ ከሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በመሆን ይሖዋን እናመሰግናለን!—ማቴዎስ 5:3