በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የራማፖ የግንባታ ስፍራ ከላይ ሲታይ። ግንባታው የሚከናወነው የተቆረጡት ዛፎች ባሉበት ስፍራ ላይ ይሆናል። ውስጠኛው ሥዕል፦ አንድ ዛፍ ቆራጭ ዛፍ እየቆረጠ

ሰኔ 6, 2023
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የዋናው መሥሪያ ቤት ፕሮጀክት በራማፖ

የራማፖን የግንባታ ስፍራ የማዘጋጀቱ ሥራ ቀጥሏል

የራማፖን የግንባታ ስፍራ የማዘጋጀቱ ሥራ ቀጥሏል

ሰኔ 1, 2023 የኒው ዮርክ ስቴት የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ዲፓርትመንት፣ በራማፖ የግንባታ ስፍራ የተቆረጡ ዛፎች እንዲነሱ ፈቃድ ሰጠ። ዛፎቹን የመቁረጡ ሥራ የተጠናቀቀው መጋቢት 18 ማለትም ዛፍ መቁረጥ የሚፈቀድበት ወቅት ከማብቃቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ነው።

የራማፖ የግንባታ ፕሮጀክት ኮሚቴ አስተባባሪ ሆኖ የሚያገለግለው ወንድም ሮበርት ማክሬድመንድ እንዲህ ብሏል፦ “እንዲህ ባሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ የምናገኘው እያንዳንዱ ፈቃድ ወደ ግንባታው አንድ እርምጃ እንደሚያቀርበን አስተውለናል። ይሖዋ ብዙ መሰናክሎችን ሲያስወግድልን ተመልክተናል፤ ወደፊትም የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንድናልፍ የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ለማየት እንጓጓለን።”—ኢሳይያስ 57:14

የግንባታ ፕሮጀክት ኮሚቴው፣ ጠቅላላው የግንባታ ዕቅድ ፈቃድ እንዲያገኝ ለማድረግ በአካባቢው ካሉ ባለ ሥልጣናት ጋር እየሠራ ነው።