በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የራማፖ ከተማ ቦርድ ስብሰባ ላይ፣ ታኅሣሥ 28, 2022

ጥር 9, 2023
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የዋናው መሥሪያ ቤት ፕሮጀክት በራማፖ

የራማፖ ከተማ ቦርድ ልዩ ፈቃድ ሰጠ

የራማፖ ከተማ ቦርድ ልዩ ፈቃድ ሰጠ

ታኅሣሥ 28, 2022 የራማፖ ከተማ ቦርድ ለራማፖ ግንባታ ፕሮጀክት ልዩ ፈቃድ ሰጥቷል። a ይህ ልዩ ፈቃድ፣ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውሉ ማለትም ለመኖሪያና ለሥራ የሚያገለግሉ ሕንፃዎች ለመገንባት ያስችለናል። ከዚህም በተጨማሪ አካባቢውን ለግንባታ ምቹ ለማድረግ ከአሁኑ የዛፍ ቆረጣ ለመጀመር ፈቃድ አግኝተናል፤ በመሆኑም ይህን ሥራ ለመጀመር የቦታ ፕላን ፈቃድ በ2023 የሚጸድቅበትን ጊዜ መጠበቅ አያስፈልገንም። ይህ ልዩ ፈቃድ፣ ለፕሮጀክቱ መጓተት መንስኤ የሚሆንብንን መሠረታዊ ነገር አስወግዶልናል።

በግንባታ ኮሚቴ ውስጥ የሚያገለግለው ወንድም ዴቪድ ሶቶ እንዲህ ብሏል፦ “ይህን ፈቃድ በማግኘታችን በጣም ተደስተናል። ቀጣዩን የግንባታ ምዕራፍ ከመጀመራችን በፊት የሚቀሩ አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩም ይሖዋ እንደ ወትሮው ሁሉ ጥረታችንን እንደሚባርከው እርግጠኞች ነን።”

የራማፖ ግንባታ የጊዜ ሰሌዳ

  1. ጥቅምት 5, 2019

    የበላይ አካሉ፣ የሚዲያ ሥራዎች በአንድ ቦታ የሚሠሩበት አዲስ ሕንፃ በራማፖ፣ ኒው ዮርክ እንደሚገነባ አስታወቀ

  2. ሰኔ 26, 2020

    ለራማፖ ከተማ ቦርድ በይፋ ማመልከቻ አስገባን

  3. ሐምሌ 8, 2020

    ከራማፖ ከተማ ቦርድ ጋር የመጀመሪያ የፕሮጀክት ስብሰባ አደረግን

  4. መጋቢት 31, 2021

    ግንባታው በሥነ ምህዳሩ ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ የሚገልጽ መነሻ ሰነድ አስገባን

  5. መጋቢት 8, 2022

    የተክሲዶ ከተማ የፕላን ቦርድ፣ የማስፋፊያ ሥራ እንዲሁም በራማፖ ሳይት መግቢያ መንገድ ላይ የማሻሻያ ሥራ እንዲካሄድ ፈቃድ ሰጠ

  6. መጋቢት 12, 2022

    መጨረሻ ያስገባነው የግንባታ የሥነ ምህዳር ተጽዕኖ ሰነድ ተቀባይነት አገኘ

  7. ኅዳር 9, 2022

    የራማፖ ከተማ ቦርድ፣ የቅይጥ የመሬት አጠቃቀም አጸደቀ

  8. ታኅሣሥ 28, 2022

    የራማፖ ከተማ ቦርድ ልዩ ፈቃድ ሰጠ፤ ይህም የቅይጥ የመሬት አጠቃቀም ማሻሻያው ሥራ ላይ እንዲውልና የጥርጊያ ሥራው እንዲከናወን መንገድ ከፈተ

  9. በእንጥልጥል ያለ

    ሙሉ የግንባታ ፈቃድ

a ይህ ፈቃድ፣ የራማፖ ከተማ ቦርድ ኅዳር 9, 2022 ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የመጣ ነው፤ ውሳኔው፣ የልዩ ፈቃድና የቦታ ፕላን ፈቃድ ማመልከቻ በተመሳሳይ ጊዜ ለማስገባት መንገድ ከፍቶ እንደነበር ይታወሳል።