በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በፊት በአዳራሽ ውስጥ የተደረገ ስብሰባ

ጥቅምት 15, 2021
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የበላይ አካሉ በአንዳንድ የተመረጡ አካባቢዎች በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎች እንደሚጀምሩ አስታወቀ

የበላይ አካሉ በአንዳንድ የተመረጡ አካባቢዎች በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎች እንደሚጀምሩ አስታወቀ

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል፣ በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎችን ለመጀመር የሙከራ ፕሮግራም እንዲያካሂዱ አንዳንድ የተመረጡ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ጋብዟል። በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉት ቅርንጫፍ ቢሮዎች አብዛኛው ሰው በተከተበባቸውና የቫይረሱ ስርጭት በጣም አነስተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ያሉ የስብሰባ አዳራሾችን ይመርጣሉ። እርግጥ ነው፣ ይህ ፕሮግራም የሚካሄደው መንግሥት መሰባሰብን በተመለከተ ያወጣቸውን ሕጎች ተከትሎ ነው። ጥቅምት 15, 2021 ይህ ማስታወቂያ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የቤቴል ቤተሰብ አባላት ተነብቧል።

የዚህ የሙከራ ፕሮግራም ውጤት ተጨማሪ ጉባኤዎች በአካል መሰብሰብ መጀመር ይችሉ እንደሆነና እንዳልሆነ ለመወሰን ይረዳል። ማስታወቂያው አክሎ እንደገለጸው በአካል የሚደረጉ ድርጅታዊ እንቅስቃሴዎች በጥቅሉ እስከ ጥር 1, 2022 ድረስ እንደተቋረጡ ይቆያሉ።

የበላይ አካሉ ለዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበር ያለውን አሳቢነት እንዲሁም ድርጅታዊ እንቅስቃሴዎችን እንደገና ለመጀመር የሚወስዳቸውን ጥንቃቄ የተሞላባቸው እርምጃዎች ከልብ እናደንቃለን። ይሖዋ የሚደረጉትን ዝግጅቶች መምራቱንና መባረኩን እንዲቀጥል እባካችሁ ጸልዩ።—ምሳሌ 14:16