በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 14, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም በሳሞአን ቋንቋ ወጣ

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም በሳሞአን ቋንቋ ወጣ

ጥቅምት 9, 2022 የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በሳሞአን ቋንቋ ወጥቷል። የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጄፍሪ ጃክሰን አስቀድሞ በተቀዳ ንግግር ላይ መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን አብስሯል፤ በአሜሪካን ሳሞአ፣ በአውስትራሊያ፣ በኒው ዚላንድ እና በሳሞአ የሚገኙ አስፋፊዎች ንግግሩን ተከታትለውታል። ንግግሩ እንዳበቃ የታተሙት መጽሐፍ ቅዱሶች ተሰራጭተዋል፤ በኤሌክትሮኒክ ፎርማት የተዘጋጀው ቅጂም ለተጠቃሚዎች ቀርቧል።

የይሖዋ ምሥክሮች በሳሞአ መስበክ የጀመሩት በ1931 ነው፤ በ1953 አፒያ ውስጥ የመጀመሪያው ጉባኤ ተቋቋመ። በ2009 አዲስ ዓለም ትርጉም በሳሞአን ቋንቋ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጣ። ትክክለኛ የሆነውና በቀላሉ የሚገኘው አዲስ ዓለም ትርጉም በአስፋፊዎችም ሆነ በቀረው ማኅበረሰብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል።

በሲዩሴጋ፣ ሳሞአ የሚገኘው የሳሞአን የርቀት የትርጉም ቢሮ

አሁን የወጣው የተሻሻለው ትርጉም በተዘጋጀበት ወቅት ትክክለኛ ሆኖም ለመረዳት ቀላልና ሰዎች በዕለታዊ ሕይወታቸው የሚጠቀሙበት ቋንቋ ለመጠቀም ተጨማሪ ጥረት ተደርጓል። አንድ ተርጓሚ እንዲህ ሲል ሐሳብ ሰጥቷል፦ “የሳሞአ ሕዝቦች ለመጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ አክብሮት አላቸው። ይህን በሚገባ የተገነዘበው የትርጉም ቡድኑ ለመረዳት ቀላል የሆነ ቋንቋ ለመጠቀም በሚያደርገው ጥረት የመልእክቱን ክብር የሚቀንስ ቃላት ላለመጠቀም ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጓል። ይሖዋ ላደረገልን እገዛ ምስጋና ይግባውና አሁን ሁላችንንም የሚጠቅም ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ተሻሽሎ በቋንቋችን ወጥቶልናል።”

ይህ ትርጉም፣ አንባቢዎች ውድ የሆኑትን የአምላካችንን የይሖዋን ሐሳቦች እንዲረዱ ያግዛል ብለን እንተማመናለን።—መዝሙር 139:17