ኅዳር 11, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና
የዋናው መሥሪያ ቤት ፕሮጀክት በራማፖ
የከተማው ቦርድ ያጸደቀው የመሬት አጠቃቀም ማሻሻያ፣ የቦታ ፕላን ፈቃድ ለማግኘት አጋጣሚ እንደሚከፍት ይጠበቃል
ኅዳር 9, 2022 የራማፖ ከተማ ቦርድ፣ መሬትን ለቅይጥ ዓላማ መጠቀምን የሚፈቅድ ማሻሻያ አጽድቋል፤ ይህን ውሳኔ ተከትሎ የራማፖ ፕሮጀክት የግንባታ ኮሚቴ፣ ልዩ ፈቃድና የቦታ ፕላን ፈቃድ ለማውጣት ማመልከት ይችላል። a
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕንፃ ተቋራጮች በራማፖ ግቢ መግቢያ ባለው መንገድ ላይ የማስፋፊያና የማሻሻያ ሥራ አከናውነዋል። በተጨማሪም የግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች ወደ ግንባታው ሳይት በሚወስደው መንገድ ላይ ያለውን ያረጀ የድንጋይ ድልድይ አድሰው ጨርሰዋል። የድልድዩ እድሳት የማስፋፊያና የማጠናከሪያ ሥራዎችን የሚጠይቅ ነበር፤ ምክንያቱም የግንባታ ዕቃዎችን የጫኑ ወይም የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን እንዲያስተናግድ ይፈለጋል። በግንባታው የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ሁሉም ተሽከርካሪዎች የሚያልፉት በዚህ ድልድይ በኩል እንደሚሆን ይጠበቃል።
የግንባታ ኮሚቴው አባል የሆነው ወንድም ማቲው ሞርዴክስኪ እንዲህ ብሏል፦ “አሁን የሰማነው የመሬት አጠቃቀም ማሻሻያ፣ ልዩ ፈቃድም ሆነ የቦታ ፕላን ፈቃድ በተመሳሳይ ጊዜ ለመጠየቅ ያስችለናል። ፈቃዱ ከተገኘ ደግሞ የጥርጊያ ሥራዎችን ታኅሣሥ 2022 ላይ መጀመር እንችላለን ብለን ተስፋ እያደረግን ነው።”
በዚህ ፕሮጀክት ላይ በቀጥታ እየተሳተፉ ያሉ ወንድሞችና እህቶች የሚያደርጉትን ጥረት ይሖዋ ‘እንዲያሳካላቸው’ ጸሎታችን ነው።—ነህምያ 1:11
a የመሬት ማሻሻያው ከመጽደቁ በፊት አካባቢው “ልዩ የመኖሪያ ቤቶች ቀጠና” ተብሎ የተመደበ ነበር