በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 4, 2020
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የክራይሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንድም አርተም ገራሲሞቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር በየነ

የክራይሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወንድም አርተም ገራሲሞቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር በየነ

የክራይሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰኔ 4, 2020 ወንድም አርተም ገራሲሞቭ ክርስቲያናዊ አምልኮውን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በማከናወኑ ምክንያት ብቻ የስድስት ዓመት እስራት በይኖበታል። ወንድም ገራሲሞቭ የያልታ ከተማ ፍርድ ቤት 400,000 ሩብል (6,000 የአሜሪካ ዶላር ገደማ) መቀጫ እንዲከፍል ያስተላለፈበት የመጀመሪያ ፍርድ እንዲቀለበስለት ጠይቆ ነበር። ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ያስተላለፈው ውሳኔ ወዲያውኑ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ወንድም ገራሲሞቭም ወደ እስር ቤት ተወስዷል። ወንድም ገራሲሞቭ ይህን ውሳኔ ይግባኝ እንደሚል ታውቋል።