በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጋቢት 5, 2020
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የክራይሚያ ፍርድ ቤት በወንድም ሰርጌ ፊላቶቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር ፈረደበት

የክራይሚያ ፍርድ ቤት በወንድም ሰርጌ ፊላቶቭ ላይ የስድስት ዓመት እስር ፈረደበት

መጋቢት 5, 2020 የክራይሚያ ሪፑብሊክ የድዝሃኮይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ፊላቶቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። ወንድም ፊላቶቭ የስድስት ዓመት እስር ተፈርዶበታል። ወንድም ፊላቶቭ፣ ክራይሚያ ውስጥ በሩሲያ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የተከሰሰ የመጀመሪያው የይሖዋ ምሥክር ነው። ወንድም ፊላቶቭ ውሳኔውን ይግባኝ እንደሚል ታውቋል።