በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጋቢት 5, 2020
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የክራይሚያ ፍርድ ቤት በወንድም አርተም ገራሲሞቭ ላይ ፈርዶ የገንዘብ ቅጣት ጣለበት

የክራይሚያ ፍርድ ቤት በወንድም አርተም ገራሲሞቭ ላይ ፈርዶ የገንዘብ ቅጣት ጣለበት

መጋቢት 3, 2020 በክራይሚያ ሪፑብሊክ የምትገኘው የያልታ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አርተም ገራሲሞቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። ወንድም ገራሲሞቭ ወደ ወኅኒ ባይገባም 400,000 ሩብል (6,000 የአሜሪካ ዶላር ገደማ) መቀጮ ተጥሎበታል። ወንድም ገራሲሞቭ ውሳኔውን ይግባኝ እንደሚል ታውቋል።