በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኢጎር ሽሚድት

ጥቅምት 25, 2021
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የክራይሚያ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ሽሚድት ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አሳለፈ

የክራይሚያ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ሽሚድት ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አሳለፈ

ወቅታዊ መረጃ | የክራይሚያ ፍርድ ቤት ይግባኙን ውድቅ አደረገ

ጥር 13, 2022 የሴቫስቶፖል ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ኢጎር ሽሚድት ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። አሁንም እስር ቤት ነው።

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 22, 2021 በሴቫስቶፖል፣ ክራይሚያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የጋጋሪንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ኢጎር ጥፋተኛ ነው በማለት በስድስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል። ወንድም ኢጎር ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ተወስዷል

  2. ሚያዝያ 22, 2021

    ጉዳዩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ታየ

  3. መጋቢት 23, 2021

    ኢጎር ከማረፊያ ቤት ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ

  4. ጥቅምት 1, 2020

    ኢጎር እገዳ የተጣለበትን ሃይማኖታዊ ድርጅት እንቅስቃሴዎች በማደራጀት ተከሶ ለሁለት ቀን በጊዜያዊ ማረፊያ ቤት ከቆየ በኋላ ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰደ

አጭር መግለጫ

ይሖዋ በሩሲያ ያሉትን ወንድሞችና እህቶች መባረኩን እንደሚቀጥልና ‘ሞገሱን’ እንደሚያሳያቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 5:12