በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከሚያዝያ 1, 2022 አንስቶ የይሖዋ ምሥክሮች ከሁለት ዓመት በኋላ የአምልኮ ቦታዎቻቸውን እንደገና ክፍት አድርገዋል

ሚያዝያ 4, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የይሖዋ ምሥክሮች በድጋሚ በአካል መሰብሰብ ጀመሩ

የይሖዋ ምሥክሮች በድጋሚ በአካል መሰብሰብ ጀመሩ

ከሚያዝያ 1, 2022 አንስቶ የይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎችን እንደገና በአካል ማድረግ ጀምረዋል። ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መጀመሪያ ላይ ትንሽ ስጋት አድሮባቸው ከነበረ እንኳ ይህ ስሜት ወዲያውኑ በሳቅ እና በደስታ እንባ ተተክቷል፤ የመንግሥቱን መዝሙሮችም በግለት መዘመር ጀምረዋል።

አንዳንዶች በስብሰባ አዳራሽ የተገኙት በሕይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በፖላንድ የሚኖረው ወንድም ክሪዚስቶቭ ሆስዞዊስኪ እንዲህ ብሏል፦ “በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በሚደረግ ስብሰባ ላይ በአካል ስገኝ ይህ የመጀመሪያዬ ነው። እውነትን የተማርኩት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ነው፤ ስጠመቅ ሥነ ሥርዓቱ በዙም ተላልፎ ነበር። በአካል ስለሚደረጉ ስብሰባዎች ብዙ ቪዲዮዎችን ስላየሁ ስብሰባዎቹ ምን እንደሚመስሉ አውቅ ነበር። በስብሰባው ላይ በግልጽ የሚታየው የወንድማማች መዋደድ፣ ደስታና ደግነት በጣም አስደሰተኝ።”

መጋቢት 2020 ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ ከተከሰተ በኋላ የይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎቻቸውን በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ማድረግ ጀመሩ። እርግጥ አሁንም ቢሆን በአካል መሰብሰብ የማይችሉ ሰዎች ስብሰባዎችን በስልክ ወይም በኢንተርኔት የመካፈል አማራጭ አላቸው።

በኤድንበርግ፣ ስኮትላንድ የሚኖረው ወንድም ኒል ካምፕቤል እንዲህ ብሏል፦ “ሙዚቃው ተከፍቶ የመክፈቻውን መዝሙር መዘመር ልክ ስጀምር ከሁለት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወንድሞቼ ጋር መልሼ በመገናኘቴ ልቤ በደስታና በአመስጋኝነት ተሞላ።”

በይሖዋ በረከት በድጋሚ በአካል መሰብሰብ በመቻላችን በጣም አመስጋኞች ነን።—መዝሙር 84:10

 

አንጎላ

አርሜንያ

አውስትራሊያ

ቼክ ሪፑብሊክ

ኢኳዶር

ጀርመን

ግሪክ

ጊኒ

ጃፓን

ካዛክስታን

ማላዊ

ኔዘርላንድስ

ፊሊፒንስ

ሩማንያ

ስኮትላንድ

ደቡብ ኮሪያ

ስፔን

ሱዳን

ታይላንድ