በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አርተም ሻብሊ

ሚያዝያ 1, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

የይሖዋ ጥበቃ ‘እንደ ግንብ አጥር’ ሆኖልኛል

የይሖዋ ጥበቃ ‘እንደ ግንብ አጥር’ ሆኖልኛል

በክራይሚያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የኬርክ ከተማ ፍርድ ቤት የካቲት 16, 2022 በዋለው ችሎት ላይ ወንድም አርተም ሻብሊ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ አሳልፏል፤ የሁለት ዓመት የገደብ እስራትም በይኖበታል። እርግጥ አሁን ወህኒ አይወርድም

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 26, 2020

    የደህንነት አባላት የአርተምን ጨምሮ በክራይሚያ የሚኖሩ አራት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። ፖሊሶቹ መስኮት ሰብረው በገቡበት ወቅት ስብርባሪው የአርተምን የአራት ዓመት ልጅ እግሩ ላይ አቁስሎታል። ለሦስት ሰዓት ያህል ብርበራ ካደረጉ በኋላ ፖሊሶቹ አርተምን ይዘውት ሄዱ፤ ጣቢያው ውስጥም ለሦስት ቀናት አቆይተውታል

  2. ሰኔ 9, 2020

    አርተም ችሎት ላይ ማስረጃ ሆኖ የሚቀርብበትን የምርመራ ሪፖርት ማየት እንዲፈቀድለት ለኬርክ ከተማ ፍርድ ቤት ጥያቄ አቀረበ። ፍርድ ቤቱ ይህን የማድረግ ሕጋዊ ግዴታ ቢኖርበትም ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል

  3. ግንቦት 24, 2021

    ችሎቱ ተሰየመ። ብዙ ወንድሞችና እህቶች ድጋፋቸውን ለማሳየት ፍርድ ቤቱ ተገኝተው ነበር፤ ውስጥ እንዲገቡ ግን አልተፈቀደላቸውም

አጭር መግለጫ

አርተም በራሱ ሕይወት እንዳየው ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን ምንጊዜም በታማኝነት ይደግፋል። በክራይሚያና በሩሲያ ላሉ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሁሉ ቋጥኝ፣ ምሽግና አስተማማኝ መጠጊያ መሆኑን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 18:2