ኅዳር 13, 2019
ዓለም አቀፋዊ ዜና
የ2019 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ከፍተኛ የተጠማቂዎች ቁጥር ያካተተ ዘገባ ይዟል
በ2019 የአገልግሎት ዓመት ውስጥ ከ300,000 በላይ ሰዎች ተጠምቀው የይሖዋ ምሥክሮች መሆናቸውን ስንገልጽላችሁ ታላቅ ደስታ ይሰማናል። ከ1999 ወዲህ ባሉት 20 ዓመታት ውስጥ የተጠማቂዎች ቁጥር ከ300,000 በላይ ሲሆን ይህ የመጀመሪያው ነው። በትጋት እያከናወንን ያለውን የስብከቱንና ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ ስለባረከው ይሖዋን እናወድሰዋለን!
የ2019 የአገልግሎት ዓመት ሌሎች ታሪካዊና የማይረሱ ክንውኖችም የተከናወኑበት ዓመት ነው። ለምሳሌ ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ተደርገዋል፣ በተለያዩ ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስ ወጥቷል እንዲሁም በዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበራችን ውስጥ ያለው ፍቅር በተግባር ታይቷል። ከዓለም አቀፉ አጠቃላይ ሪፖርት ላይ የተወሰነው ከዚህ በታች ቀርቧል። a
ሪፖርቱ ውስጥ የተካተቱ አገሮች ብዛት፦ 240
በዓለም ዙሪያ በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ፦ 20,919,041
ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር፦ 8,683,117
አጠቃላይ ተጠማቂዎች፦ 303,866
እንዲህ ያሉ አስደሳች ሪፖርቶችን መስማታችን በ2020 የዓመት ጥቅሳችን ላይ የሚገኘውን ጌታችን ኢየሱስ የሰጠንን ‘ሂዱና ከሁሉም ብሔራት ሰዎችን እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው’ የሚለውን ትእዛዝ ተግባራዊ እንድናደርግ ያነሳሳናል።—ማቴ. 28:19
a የ2019 የይሖዋ ምሥክሮችን የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት የያዘ ዘገባ jw.org እና JW ላይብረሪ ላይ በቅርቡ ይወጣል።