በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኃይለኛ ነፋስና ከፍተኛ ዝናብ የቀላቀለችው ፊዮና የተባለችው አውሎ ነፋስ ከፍተኛ ጉዳት አስከትላለች

መስከረም 26, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ፊዮና የተባለችው አውሎ ነፋስ በካሪቢያን ከባድ ጉዳት አስከትለች

ፊዮና የተባለችው አውሎ ነፋስ በካሪቢያን ከባድ ጉዳት አስከትለች

መስከረም 18, 2022፣ ፊዮና የተባለችው አውሎ ነፋስ በፖርቶ ሪኮና በአቅራቢያዋ በሚገኙ ደሴቶች ላይ ጉዳት አደረሰች። ነፋሱ በሰዓት እስከ 160 ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት ይነፍስ የነበረ ሲሆን 75 ሴንቲ ሜትር የሚያክል ዝናብ ዘንቧል። አውሎ ነፋሱ መንገዶችንና ድልድዮችን ያወደመ ከመሆኑም በላይ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥባቸው አድርጓል። በመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ የተከሰተው ጉዳት ባለሥልጣናት በአደጋው ለተጎዱ ሰዎች ምግብ፣ ውሃና መድኃኒት ማድረስ ከባድ እንዲሆንባቸው አድርጓል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

ፖርቶ ሪኮ፣ ሴንት ኪትስ እና ኔቨስ፣ ተክስ እና ኬይኮስ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የሞተ የለም

  • 4 አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 75 አስፋፊዎች ተፈናቅለዋል

  • 140 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 18 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 ቤት ወድሟል

ዶሚኒካን ሪፑብሊክ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የሞተ የለም

  • 58 አስፋፊዎች ተፈናቅለዋል

  • 57 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 26 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 ቤቶች ወድመዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

ጓዴሎፕ እና ማርቲኒክ

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የሞተ የለም

  • 16 አስፋፊዎች ተፈናቅለዋል

  • 43 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 2 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 13 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች እረኝነት እያደረጉና ተግባራዊ እርዳታ እየሰጡ ነው

  • በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች ሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠትና ቤታቸውን ለመጠገን አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

በአደጋው የተጎዱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የወንድማማች ማኅበሩ ባሳያቸው ፍቅር እንደተጽናኑ እርግጠኞች ነን።—የሐዋርያት ሥራ 11:29