በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 30, 2021
ዓለም አቀፋዊ ዜና

JW.ORG ላይ አዲስ የገጽታ ማስተካከያ ወጣ

JW.ORG ላይ አዲስ የገጽታ ማስተካከያ ወጣ

በቅርብ ጊዜ jw.org ላይ ከተደረጉት ማስተካከያዎች አንዱ ብዙ ተጠቃሚዎች ሲጠይቁ የነበሩት ነገር ነው። አሁን ድረ ገጹ ላይ ነጭ ወይም ጥቁር ገጽታ እንዲኖር መምረጥ ይቻላል።

ጥቁሩ ገጽታ (ጥቁር እይታ ወይም የጨለማ እይታ) ላይ ነጣ ያሉ ጽሑፎችና ምስሎች በጥቁር መደብ ላይ ይታያሉ። አንዳንድ ተጠቃሚዎች የስክሪኑን ብርሃን ስለሚቀንስላቸው ይህን አማራጭ ይመርጣሉ። ይህ ገጽታ፣ በተለይ ምሽት ላይ ወይም አነስተኛ ብርሃን ባለባቸው አካባቢዎች ስታነቡ ዓይናችሁ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ ሊረዳ ይችላል። በተጨማሪም ውስን የሆነ የማየት ችሎታ ያላቸውን ወይም ደማቅ ብርሃን ለማየት የሚቸገሩ ሰዎችን ሊጠቅም ይችላል።

የገጽታ ማስተካከያዎቹን ለማግኘት ገጹ ላይ ወደ ታች ውረዱና “የገጽታ ማስተካከያ” የሚለውን ተጫኑ። jw.org የመሣሪያችሁን የእይታ አማራጭ እንዲከተል የምትፈልጉ ከሆነ “ሲስተም” የሚለውን ምረጡ። jw.org በማንኛውም ጊዜ አንድ ዓይነት ገጽታ እንዲጠቀም ከፈለጋችሁ ደግሞ “ነጭ” ወይም “ጥቁር” የሚለውን ምረጡ።

እነዚህ አዲስ ገጽታዎች JW ላይብረሪ አፕሊኬሽን ላይ ገና አልተካተቱም። የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ በምናገኝባቸው የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችን ላይ ለሚደረገው ቀጣይ ማሻሻያ ይሖዋን እናመሰግነዋለን።