በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚያዝያ 20, 2022
ዚምባብዌ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ቋንቋ ወጣ

የዚምባብዌ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ጆን ሁንጉካ ሚያዝያ 10, 2022 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ቋንቋ መውጣቱን አበሰረ። አስቀድሞ የተቀረጸው ፕሮግራም 500 ገደማ ለሚሆኑ ሰዎች ተሰራጭቷል። የታተመውን መጽሐፍ ቅዱስ ከሐምሌ 2022 ጀምሮ ማግኘት ይቻላል።

የቺቶንጋ ቋንቋን በዋነኝነት የሚናገሩት በዛምቢያ ደቡባዊና ምዕራባዊ ግዛቶች እንዲሁም በሰሜናዊ ዚምባብዌ የሚኖሩት የቶንጋ ሕዝቦች ናቸው። በ2014 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በቺቶንጋ (በዛምቢያ በሚነገረው) ወጥቶ ነበር፤ ይህ በዚምባብዌ ከሚነገረው ቺቶንጋ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ቋንቋ ነው። ሆኖም በቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ ሲተረጎም አሁን የመጀመሪያ ጊዜው ነው። ከዚህ ቀደም የቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ተናጋሪዎች በዛምቢያ በሚነገረው ቺቶንጋ የተተረጎሙ መጽሐፍ ቅዱሶችን ለመጠቀም ይገደዱ ነበር።

የዛምቢያው ቺቶንጋ እና ቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ተመሳሳይነት ቢኖራቸውም የአንዳንድ ቃላትና ሐረጎች ትርጉም በጣም የተለያየ ነው። ለምሳሌ በዛምቢያው ቺቶንጋ በተዘጋጀው የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ 1 ዮሐንስ 3:17 አንድ ክርስቲያን ‘ለተቸገረ’ ወንድሙ ሊራራለት እንደሚገባ ይናገራል። ሆኖም በቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ቋንቋ ይህ አገላለጽ “አእምሮውን የሳተ” የሚል ትርጉም ያስተላልፋል። በመሆኑም የትርጉም ቡድኑ ለቋንቋው ተናጋሪዎች ትክክለኛውን ትርጉም በሚያስተላልፍ መልኩ አገላለጹን አስተካክሎታል።

በቢንጋ፣ ዚምባብዌ የሚገኘው የቺቶንጋ (ዚምባብዌ) የርቀት የትርጉም ቢሮ ከሚጠቀምባቸው ሕንፃዎች አንዳንዶቹ

አንዱ ተርጓሚ እንዲህ ብሏል፦ “ቀደም ሲል አገልግሎት ስወጣ በጥቅሶቹ ውስጥ ያሉትን ቃላት ትርጉም ለማነጋግራቸው ሰዎች በማብራራት ብዙ ጊዜ አጠፋ ነበር። አሁን ግን ጥቅሱን ሳነበው የአምላክ ቃል ወዲያውኑ ይገባቸዋል።”

የቺቶንጋ (ዚምባብዌ) ተናጋሪ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ይህን አዲስ መጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመው “የሕይወትን መንገድ” ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ላላቸው ሰዎች ማሳወቅ በመቻላቸው በጣም ተደስተናል።—መዝሙር 16:11