በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 29, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ

ሂዩስተን፣ ዩናይትድ ስቴትስ (ስፓንኛ)—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ሂዩስተን፣ ዩናይትድ ስቴትስ (ስፓንኛ)—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከነሐሴ 23-25, 2019

  • ቦታ፦ በሂዩስተን፣ ቴክሳስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ኤን አር ጂ ስታዲየም

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 56,167

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 626

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,500

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ስፔን፣ ማዕከላዊ አሜሪካ፣ ቦሊቪያ፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ ቺሊ፣ አርጀንቲና፣ ኢኳዶር፣ ኮሎምቢያ፣ ዶሚኒካን ሪፑብሊክ፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ፊሊፒንስ፣ ፔሩ፣ ቬኔዙዌላ

  • ተሞክሮ፦ የሂዩስተን የጠፈር ማዕከል የሽያጭ ኃላፊ የሆነችው ጆኤል ሃርዲን እንዲህ ብላለች፦ “ዛሬ ጠዋት [ልዑካኑ ወደ ሕንፃው ሲገቡ ቲኬት የምትቀበለው ሠራተኛ] ወደ እኔ መጥታ ‘ጆኤል . . . ሁሉም ሰው ዓይን ዓይኔን እያየ “አመሰግናለሁ” ብሎኛል፤ እንዲያውም አንዳንዶቹ በተለያየ ቋንቋ ነው ያመሰገኑኝ’ አለችኝ። በጣም ደስ ብሏት ነበር። እንደዚያ ተደስታ ካየኋት ቆይቻለሁ።”

 

ልዑካኑ ጠዋት ላይ ወደ ስታዲየሙ ሲደርሱ

ልዑካኑ ከአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ጋር ሲሰብኩ

በሺዎች የሚቆጠሩ ፈቃደኛ ሠራተኞች የዓርቡ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ኤን አር ጂ ስታዲየምን ሲያጸዱ

በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 626 ወንድሞችና እህቶች መካከል ሁለቱ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ማርክ ሳንደርሰን ዓርብ ከሰዓት የመደምደሚያውን ንግግር ሲያቀርብ

ልዑካኑ ማስታወሻ እየያዙ ፕሮግራሙን ሲከታተሉ

አንዲት እህት ለልዑካኑ ከተዘጋጁት ጉብኝቶች አንዱ የሆነውን የሂዩስተን የተፈጥሮ ሳይንስ ቤተ መዘክርን ስታስጎበኝ

ወንድሞችና እህቶች ምሽት ላይ በተደረገው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ ውዝዋዜ ሲያቀርቡ

እሁድ ቀን በስብሰባው መደምደሚያ ላይ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሜዳው ላይ ሆነው በካሜራው ፊት እጃቸውን ሲያውለበልቡ