ሐምሌ 19, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ
ሂዩስተን፣ ዩናይትድ ስቴትስ (እንግሊዝኛ)—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከሐምሌ 12-14, 2019
ቦታ፦ በሂዩስተን፣ ቴክሳስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ኤን አር ጂ ስታዲየም
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ እንግሊዝኛ፣ ኮሪያኛ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 50,901
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 401
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,000
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሕንድ፣ ስካንዲኔቪያ፣ ቤልጅየም፣ ብሪታንያ፣ ብራዚል፣ ቼክ ስሎቫክ፣ አውስትራሌዢያ፣ ካናዳ፣ ኮሎምቢያ፣ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ፊሊፒንስ
ተሞክሮ፦ የሂዩስተን ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሲልቨስተር ተርነር ለስብሰባው ወደ ሂውስተን በመጡት 50,000 የይሖዋ ምሥክሮችና በእንግዶቻቸው በጣም ተገርመው ነበር። እንዲህ ብለዋል፦ “ንጹሕ አየር የተነፈስኩ ያህል ሆኖ ተሰምቶኛል። በራችን ለእናንተ ክፍት የሆነው ለዚህ ነው። ወደ ሂዩስተን ከተማ በዓመት ሁለቴ ብትመጡ እንኳ ሞቅ አድርገን እንቀበላችኋለን። ከዚህ በኋላ በየዓመቱ ኑ!”
ወንድሞችና እህቶች ወደ ሂዩስተን የመጡትን ልዑካን ሲቀበሉ
ልዑካኑ ከአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ጋር ሲሰብኩ
ከ401 ተጠማቂዎች መካከል የተወሰኑት
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም አንቶኒ ሞሪስ የቅዳሜውን ስብሰባ የመጨረሻ ንግግር ሲያቀርብ
የባሕል ልብስ የለበሱ ልዑካን ፎቶግራፍ ሲነሱ
ልዑካኑ እርስ በርስ ሲጨዋወቱ
የልዩ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እሁድ ቀን ስብሰባው ሲያልቅ ሕዝቡን ሲሰናበቱ
የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ምሽት ላይ በነበረው ፕሮግራም ላይ ከመድረክ አዝናኝ ዝግጅቶችን ሲያሳዩ፤ ዘፈንና ውዝዋዜ እንዲሁም የይሖዋ ምሥክሮች በሂዩስተን ያሳለፉት ታሪክ በአጭሩ ቀርቦ ነበር