በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 7, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

ሎራ የተባለችው አውሎ ነፋስ ሉዊዚያናን መታች

ሎራ የተባለችው አውሎ ነፋስ ሉዊዚያናን መታች

ቦታ

አርከንሶ፣ ሚሲሲፒ፣ ምዕራባዊ ሉዊዚያና እና ምሥራቃዊ ቴክሳስ

የደረሰው አደጋ

  • ሎራ የተባለችው አውሎ ነፋስ ነሐሴ 27, 2020 ምዕራባዊ ሉዊዚያናን የመታች ሲሆን ከፍተኛ የንብረት ጉዳትና የኃይል መቋረጥ አስከትላለች

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • አንዲት አረጋዊት እህት ከአደጋው ለማምለጥ ሲባል ከነበሩበት የሕክምና ተቋም ወደ ሌላ ቦታ እየተጓጓዙ በነበረበት ወቅት ሕይወታቸው አልፏል

  • አንዲት ሌላ እህት ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶባታል

  • 3,992 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 10 የወንድሞቻችን ቤቶች ወድመዋል

  • 95 ቤቶችና 4 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 192 ቤቶችና 16 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ አስፋፊዎች ማረፊያ እንዲያገኙ ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ነው

ተሞክሮዎች

  • በአካባቢው የሚኖሩ ወንድሞች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ አስፋፊዎችን አሳርፈዋል፤ ይህን ያደረጉት ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ የደህንነት ደንቦችን በጠበቀ መልኩ ነው። ከመኖሪያው ተፈናቅሎ መጠለያ ያገኘ አንድ ወንድም እንዲህ ብሏል፦ “ይህን ሁሉ ነገር የይሖዋ በረከት እንደሆነ አድርገን እንመለከተዋለን!”

በአውሎ ነፋሱ በተጠቁት አካባቢዎች የሚኖሩት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መመሪያ በመከተልና የተቸገሩትን በመርዳት ‘ራሳቸውን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች አድርገው እያቀረቡ ነው።’—2 ቆሮንቶስ 6:4